በመዲናዋ በአገልግሎት ብዛትና ከአጠቃቀም ጉድለት ጉዳት ለደረሰባቸው ድልድዮች ጥገና እየተደረገ ነው

በመዲናዋ በአገልግሎት ብዛትና ከአጠቃቀም ጉድለት ጉዳት ለደረሰባቸው ድልድዮች ጥገና እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በአገልግሎት ብዛትና ከአጠቃቀም ጉድለት ጉዳት ለደረሰባቸው ድልድዮች ጥገና እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ ድልድዮች እና የድጋፍ ግንቦችን የጉዳት መጠናቸውን በመለየት የጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ጊዮን ሆቴል፣ ልደታ ፀበል አካባቢ፣ ከጤና ሚኒስቴር- ጨፌ ሜዳ፣ አንፎ አልፋ ትምህርት ቤት፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ አርሴማ ድልድይ፣ እግዚአብሄር አብ አካባቢ፣ አምቼ አካባቢ፣ መነን ወረዳ 13 እና መነን አካባቢ ድልድዮች የጥገና ስራ መጠናቀቁንም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በቀጣይም በተለያዩ አካባቢዎች ጥገና የሚያስፈልጋቸው ድልድዮች የጥገና ስራ እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው፡፡

ህብረተሰቡም ድልድዮችን ለጉዳት ከሚያጋልጡ ህገወጥ ድርጊቶች እንዲቆጠብ ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በመዲናዋ በአገልግሎት ብዛትና ከአጠቃቀም ጉድለት ጉዳት ለደረሰባቸው ድልድዮች ጥገና እየተደረገ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply