በመዲናዋ ዓለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ተከፈተ

ሐሙስ ኀዳር 1 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከ270 በላይ የአገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አለምአቀፍ የማዕድን ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በሚሊንየም አዳራሽ በይፋ ተከፍቷል።

በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይም የኢፌዴሬ ፕሬዚዳንት ሳህለወቅር ዘውዴ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል፡፡  አለምአቀፍ የማዕድን ኤክስፖው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ኀዳር 3 ቀን 2015 እንደሚቆይ የተነገረ ሲሆን፤ በዚህም የማዕድን ኩባንያዎች፣ የጌጣጌጥ አምራቾችና ላኪዎች፣ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት እንደሚሳተፉበት ተነግሯል።በተጨማሪም ኤክስፖው አምራቾችን ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ገዢዎች ጋር እንዲሁም፤ አምራቾችና ላኪዎችን ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቀጥታ ያገናኛል ተብሏል።

ከውጪ የሚመጡ የማዕድን ኩባንያዎች በኤክስፖው ላይ መሳተፋቸው በትዮጵያ ያለውን የማዕድን ኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲመለከቱና የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ እድል እንደሚፈጥርም መገለጹም ከማዕድን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡በኤክስፖው የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾች መሳተፋቸው ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የመተዋወቅ እድል ከመፍጠሩም በላይ የኢትዮጵያ የማዕድን እምቅ ኃብት የአሁን ገፅታ እና የወደፊት ተስፋ ይገልጻል ተብሎም ይጠበቃል።

The post በመዲናዋ ዓለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ተከፈተ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply