ሐሙስ ግንቦት 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መንግሥት ያወጣውን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ በመተላለፍ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ የማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር ተደጋጋሚ ውይይት ማድረጉን ያስታወሰ ሲሆን፤ የተሰጡ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያዎችን በተላለፋ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
በዚህም እርምጃው የተወሰደባቸው በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙና አለአግባብ ከተተመነው የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ፣ ምርት በመደበቅ መሸጫ ቦታቸውን ዘግተው በመጥፋት የተገኙ ሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የተጀመረውን አሰራር የማስጠበቅ ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
The post በመዲናዋ የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ በመተላለፍ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ first appeared on Addis Maleda.
Source: Link to the Post