በመዲናዋ ያለውን የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር ያቃልላል የተባለ መተግበሪያ በስራ ላይ ዋለ፡፡በከተማዋ ያለውን የትራንሰፖረት ችግር በመረዳት ለህበረተሰቡ እንደመፍትሄ ሆኖ የቀረበው ሴፍ መተ…

በመዲናዋ ያለውን የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር ያቃልላል የተባለ መተግበሪያ በስራ ላይ ዋለ፡፡

በከተማዋ ያለውን የትራንሰፖረት ችግር በመረዳት ለህበረተሰቡ እንደመፍትሄ ሆኖ የቀረበው ሴፍ መተግበሪያ ማንኛውም ተጓዥ በጋራ መጠቀም ሚያስችል መተግበሪያ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

ማህበረሰቡ የሴፍ መተግበሪን በቀላሉ በመጠቀም ካስፈለገ በግል ካስፈለገ በቡድን በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚቻል ሲነሳ ክፍያውም የሚደርስበትን በግል መክፈል እንደሚችል ተገልጣል፡፡

አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎቱን ክፍት እንዳደረገ የገለጠው ሴፍ ተጠቃሚው ማህበረሰቡም ለተለያዩ ወንጀሎች እና አደጋዎች እንዳይጋለጥ እንደሚረዳው ተነስቷል፡፡

የከተማውን የትራንስፖርት እጥረት በተወሰነ መጠን ከመቅረፉም ባሻገር ተጓዦች አብረዋቸው ከሚጓዙት ጋር የትራንስፖርት ክፍያውን በመጋራት ወጪያቸውን የሚቀንሱበትን ሂደት እንደፈጠረመረ ተገልጧል፡፡

መተግበሪያው ላይ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ወይም የጥሪ ማዕከሉን ተጠቅመው ጉዞ ሲያደርጉ ከእያንዳንዱ ጉዞ 5% የጉዞዋቸውን ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያገኙም ተነግሯል።

መተግበሪያው ላይ የሚያገኙትን የሪፈራል ኮዶችንም በመጠቀም ተጠቃሚዎች ሌሎች ተጠቃሚዎችን በመጋበዝ ከእያንዳንዱ ጉዞዎቻቸው 2% ኮሚሽን ማግኘት እንደሚችሉም ተነስቷል።

ተጠቃማች ሴፍን ሲጠቀሙ “share my location” የሚለውን በመጠቀም
አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻልም ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም አንድ አሽከርካሪ ደህንነት ካልተሰማው መተግበሪያ ላይ ያለውን የ”SOS” ምልክት በመንካት አስር የአደጋ ጊዜ ጥሪዎች በአቅራቢያው ላሉ የአሽከርካሪዎች ስልክ ቁጥሩ ያካተተ የአደጋ ጥሪዎችን መላክ እንደሚችሉም ተነስቷል፡፡

በለዓለም አሰፋ

የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply