“በመድሃኒያለም ፍቃድ በኦነጎች ከተርከፈከፈብኝ የጥይት አረር ተርፌያለሁ!”  ከኦነግ አሰቃቂ ግድያ የተረፈው ዲያቆን ደሳለኝ ሰፊው ከአሶሳ  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…  የካቲት 24 ቀን…

“በመድሃኒያለም ፍቃድ በኦነጎች ከተርከፈከፈብኝ የጥይት አረር ተርፌያለሁ!” ከኦነግ አሰቃቂ ግድያ የተረፈው ዲያቆን ደሳለኝ ሰፊው ከአሶሳ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… የካቲት 24 ቀን…

“በመድሃኒያለም ፍቃድ በኦነጎች ከተርከፈከፈብኝ የጥይት አረር ተርፌያለሁ!” ከኦነግ አሰቃቂ ግድያ የተረፈው ዲያቆን ደሳለኝ ሰፊው ከአሶሳ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዲያቆን ደሳለኝ ሰፊው ይባላል፤ በአሶሳ ብድርና ቁጠባ ተቋም እየሰራ ይገኛል። የብድርና ቁጠባ ባለሙያዎቹ ዲያቆን ደሳለኝና ጌታቸው ስጦታው ከአሶሳ ተነስተው ለኦዲት ስራ ወደ ሴዳል ወረዳ አቅንተው ስራቸውን አጠናቀው በመለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሲመለሱ የገጠማቸውን ለማመን ተቸግረዋል፤ ግን ፀጉራቸውን ቁጥርጥር ከተሰሩ ከዘር አጥፊና ዘራፊ የኦነግ ታጣቂዎች ጋር መፋጠጥ የግድ እንደሆነባቸው ተነግሯል። የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከሴዳል ወደ አሶሳ በጉዞ ላይ እያሉ ምዕራብ ወለጋ መንዲ አካባቢ ሀሮ በተባለ ቀበሌ ሲደርሱ ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ እስከአፍንጫቸው በታጠቁ ኦነጎች ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመኪና እንዲወርዱ ትዕዛዝ ሰጡ። ከእነሱ ቀደም ብሎ የደረሰ ሌላ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻንም በማስቆም 2 ሰዎችን መርጠው በማስወረድ አስቀርተዋል። እነ ዲያቆን ደሳለኝ ከተሳፈሩበት መኪና መታወቂያ በማየት 7 ሰዎችን በመለየት እንዲሁም ከሲኖትራክ የነበሩ 2 በድምሩ 11 ተሳፋሪዎችን “እናንተ ካብኒ/አመራር ናችሁ”በማለት አግተው ወደ ጫካ ወስደዋቸዋል። የብድር እና ቁጠባ ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም አመራር አለመሆናቸውን ይልቁንስ ተቋማቸው ከፖለቲካ ንክኪ የሌለው ስለመሆኑ ቢያስረዱም ከጨካኝ አጋቾች አንድም ለመረዳት የፈለገ አካል አልተገኘም፤ ቀጥል እያሉ ወደ ጫካ መውሰዳቸውን ቀጥለዋል። ብዙ ከተጓዙ በኋላ አሸባሪዎቹ 2 ሾፌሮችን እንዲመለሱ በማድረግ 9 ተሳፋሪዎችን አስቀርተው ለሌላ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አስረከቡ፤በግምት ከምሽቱ 4 ሰዓት ይሆናል። በማግስቱ የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ንጋት ላይ ሌላ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወደ ታጋቾቹ መጥተዋል፤ ምክንያቱም ካብኒ ተይዟል በሚል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ እስከ ላይኛው የዘር አጥፊው ቡድን አመራር ድረስ ቀድሞ መረጃው ደርሷልና። የጫካው ምርመራ ቀጠለ ፤ ብሄራቸው፣ የተወለዱበት አካባቢና የስራ መደብ ተጠይቀዋል። እነ ዲያቆን ደሳለኝ፣ጌታቸው፣ ዘሪሁንና አረጋ የተባሉ ታጋቾች አማራ መሆናቸውን ተናገሩ፤የተወለዱበትን አካባቢ ጨምረውና አሁን ላይ የትና ምን እንደሚሰሩ በግልፅ አስረድተዋል፤ አስመዝግበዋል። “ዞሮ ዞሮ አይዟችሁ፤ ምንም አትሆኑም፤ እኛ አመራር ናችሁ ተብሎ ነው የተሰጠን መረጃ፤ መጀመሪያ የያዟችሁ ሰዎች የተሳሳተ መረጃ ነው የነበራቸው” በሚል ከመረሸኛው ቦታ እስኪደርሱ የሚታልል ገዳይም ነበር። “አላማችን ሰውን አስተምሮ መላክ እንጅ በሰው ላይ ሌላ ጉዳት አናደርም” ሲሏቸውም ከታጋቾች መካከል”አይ ጥሩ ነው፤ በሚዲያ ብዙ ነገር ነበር የምንሰማው፤እዚጋ ግን በተግባር ስናይ በቃጥሩ ነገር ነው፤ በዚሁ ከቀጠላችሁ ጥሩ ነው።” በማለት አስተያየት የሰጠም አለ። ለአሸባሪዎቹ ከምግብና ውሀ ጀምሮ ሌሎች ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብላቸው፣የሚደዋወላቸውና መረጃ የሚያቀብላቸው አካል አላጡም፤ በየጫካው እየተሹለከለከ ለአማራው ማረጃ እያቀበለ ነው። ታጋቾችን በጥቅምት 2013 ዓ.ም አማራው በጅምላ ወደተረሸነበት ምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ወስደዋቸዋል፤ ዲላ ከሚባል ወንዝ አካባቢ አሳርፈዋቸዋል። ቅብብሉ ቀጥሏል ፤ አንደኛው ገዳይ ለሌላኛው አሳልፎ በመስጠት አሁንም በጉዞ ላይ ናቸው። በማይሰጉት ቦታ ቀን በሚሰጉት አካባቢ ደግሞ በሌሊት እንዲጓዙ ያደርጋሉ። አርብ የካቲት 5 ተይዘው ምርመራው በተደረገበት ቅዳሜ በሳምንቱ በ8ኛ ቀናቸው እንደገና በ4ቱ ታጋቾች ላይ ምርመራው ተደርጓል። ከ5ቱ ታጋች ኦሮሞዎች መካከል 4 ጠርተው ከጠየቁ በኋላ ለሁሉም የያዙባቸውን ሞባይል እና ገንዘብ በመመለስ በሰላም ግቡ በማለት መንገድ በማሳየት ሸኟቸው። ላብቶፓቸው እና ስልካቸው ተይዞ እንደሚለቀቁ የሚያመለክት የተስፋ መልዕክት ነግረው 5ቱን ኦሮሞዎች ከለቀቁ በኋላ በአማራዎች ላይ የጭካኔ እርምጃ ሲወስዱ ብዙ አልቆየም። ቅዳሜ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት አካባቢ የብድርና ቁጠባ ባለሙያዎች ዲያቆን ደሳለኝ፣ና ጌታቸው ስጦታው፣ የውሃ ባለሙያው ዘሪሁን እና ከካማሼ ዞን ሲሰራ ቆይቶ በዝውውር ወደ ሴዳል ወረዳ በዝውውር የመጣውን የባህር ዳር አካባቢ ልጅ አረጋ የተባሉ አማራዎችን ይዘው ወደ ወንዝ ዳር በመውሰድ “ተንበርከኩ አሉ፤ በሆዳችሁም ተደፉ”ሲሉ ትዕዛዝ ሰጧቸው። በነፍሰ ገዳዮች የታጠሩት ታጋች አማራዎችም ወደ ማን ይጮሃሉ፤ ወደ ፈጣሪ እንጅ። የተባሉትን ትዕዛዝ ፈፀሙ። በቃ ሰዋዊ አውሬዎቹ ኦነጎቹ አርከፈከፉባቸው። በላያቸው ላይ የጥይት ማዕት አዘነቡባቸው። ተፈፀመ። ከመካከላቸው ግን በእግዚአብሄር ኃይል የተረፈ አለ። ጭንቅላቱና አንገቱትን አካባቢ በቀላል የቆሰለው የአሶሳ ብድርና ቁጠባ ባለሙያው ዲያቆን ደሳለኝ ወደቀ፤ ፀጥም አለ። ከዛም አሸባሪዎቹ፣ ፀረ አማራዎቹ፣ከኦሮሞ ማህፀን የተፈጠሩት ጉዶቹ፣ ኦነጎቹ ጥይቱን የሰማ አካል ይመጣብናል በሚል ፍርሃትና ሁሉንም ገድለናል በሚል እሳቤ ጥለዋቸው ሸሹ። ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ራሴን ስቸ ከወደቅሁበት ነፍስ ዘራልኝ፤ ዞሬም 3ቱ መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ይለናል፤ በየሄድንበት ሁሉ 7 ጊዜ ሰላም ለኪ እና ፀሎተ እግዝተነ ማርያም አደርስ ነበር ያለው ዲያቆን ደሳለኝ ነው። ለ3 ቀናት ያህል በምግብ የተቀጣው ዲያቆኑ ከተተኮሰበት የጥይት አረር ተርፎ ለማናገር በቅቷል፤ ቁስሉም ቀላል በመሆኑ አሁን ላይ ተሽሎት ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል መብቃቱን ለማረጋገጥ ተችሏል! ጫካ ለጫካ እየተጓዝኩ አድሬ፣ በመድሃኒያለም ፍቃድ መንገዴን እሱ እየመራኝ ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ዋሽንፋ ገባሁ፤ ከዛም የኪዳነ ምህረት ዋዜማ እለት የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም ጫላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ደርሼ ሰዎችን በመለመን የተዋጣልኝን 157 ብር ይዠ ቤተሰብ መታወቂያ እንዲላክልኝ ካደረኩ በኋላ በነጆ በኩል አድርጌ ወደ አሶሳ ባንባሲ ወረዳአቅንቸ ከቤተሰቦቼ ጋር ተቀላቅያለሁ ብሏል። እንኳንም ከዛ ሁሉ ስቃይ ወጥተህ በሰላም ቤተሰቦችህን ተላቀልክ! እንኳንም መድሃኒያለም እረዳህ! በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችን ነፍስ ይማር!_አሚማ! ዝርዝሩን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply