በገና በዓል ከመርሀ ግብሩ ውጪ ታሪፍ በመጨመር ከተፈቀደው በላይ በመጫን ከመርሃ ግብሩ ውጪ በሌላ መስመር በሰሩ አሸከርካሪዎች ቅጣት መጣሉን የባለስልጣኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለአሐዱ ገልፀዋል፡፡
ከመናኻሪያ ውጪ ከተፈቀደላቸው በላይ እንዳይጭኑ እና ከታሪፍ በላይ እንዲያስከፍሉ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ጠቅሰው ችግሩን ለመቅረፍ ከመንገድ ደህንነት ተቆጣጠሪዎች ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡አክለውም የትራንስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር በተለይም ችግር እንደሚያጋጭማቸው ተጨማሪ ተሸከርካሪዎች እንደተዘጋጁ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ማንኛውም ተሳፋሪ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ካላደረጉ እንደማይስተናገዱ ገልፀዋል፡፡
ቀን 07/05/2013
አሐዱ ሬዲዮ 94.3
Source: Link to the Post