በመጪው ሐሙስ የሚጀመረውን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አስመልክቶ ምክክር ተካሄደ

በመጪው ሐሙስ የሚጀመረውን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አስመልክቶ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዳር 24 ቀን የሚጀመረውን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ምክክር መካሄዱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ምክክሩ በፈተና ጣቢዎች ሊደረጉ በሚገቡ የግብዓት ዝግጅቶች፣ በጸጥታ፤ በኮቪድ 19 እና በበጀትና ሌሎች አስፈላጊ በሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ነው ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

የመዲናዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በቢሮው ስር ያለው የትምህርት መዋቅር ከታች ጀምሮ እያደረገ ያለውን ዝግጅት አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም በጸጥታ አካላት በኩል ያለውን ዝግጅት ለመገምገምና የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ምክክሩ መካሄዱን ጠቅሰዋል፡፡

በትምህርት ቢሮው ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የፈተና አስተዳደር ማስፈፀሚያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

ከፈተና ዕቅድ ጀምሮ በፈተና አስተዳደር ሂደት ያሉ መልካም ተሞክሮዎችና ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረው ሰነድ በዋናነት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ የፈተና ሂደቶች ላይ በየደረጃው ያሉ የፈተና አስፈፃሚ አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችም ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከወላጆችና የትምህርት ቤት አካባቢ ማህበረሰብ ጀምሮ በተማሪዎች ሊደረጉ ስለሚገቡ ተሳትፎዎችና ተባባሪነትን መካተት ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

The post በመጪው ሐሙስ የሚጀመረውን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አስመልክቶ ምክክር ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply