በመጪው ሐሙስ  የግዮን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በግሽ ዓባይ ከተማ ይከበራል፡፡ (አሻራ ጥር 10፣ 2013 ዓ.ም)  የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነችው በግሽ ዓባይ ከተማ የግዮን ቀን ይከ…

በመጪው ሐሙስ የግዮን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በግሽ ዓባይ ከተማ ይከበራል፡፡ (አሻራ ጥር 10፣ 2013 ዓ.ም) የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነችው በግሽ ዓባይ ከተማ የግዮን ቀን ይከ…

በመጪው ሐሙስ የግዮን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በግሽ ዓባይ ከተማ ይከበራል፡፡ (አሻራ ጥር 10፣ 2013 ዓ.ም) የታላቁ ዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነችው በግሽ ዓባይ ከተማ የግዮን ቀን ይከበራል፡፡ አባይ ከጣና ሀይቅ በ160 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ ሰከላ- ግሽ ዓባይ ላይ ይመነጫል፡፡… ምንጩ ገባሮችን እየሰበሰቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ 800 ኪሎሜትር ያህል ይጓዛል፡፡ በአጠቃላይ በዓለም ላይ ከ6 ሺ ኪሎሜትር በላይ በመጓዝ የዓለም ረጅሙ መንገደኛ ውሃ ነው፡፡ ግብፅ ናይል ከምትለው 85 ከመቶው ኢትዮጵያ የምታመነጨው ነው፡፡ የዚህ ታላቅ ወንዝ መነሻ የሆነችው ግሽ ዓባይ የግዮንን በዓል ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ፖለቲካዊ እና ታሪካዊ ዳህራውን በመተንተን እና ማህበራዊ እሴቱን በማሳየት በዓሉ ይከበራል፡፡ በዓሉ ሰከላ የምትታወቅበት አትሌቲክስ መንደር የሚጎበኝ ሲሆን የአየር ንብረቱ እና መልካዓምድሩ ሰከላን ለአትሌቲክስም ተመራጭ አድርጓታል፡፡ በርካታ አትሌቶችም ከሰከላ ፈልቀዋል፡፡ እነ ውዱ አያሌው የሰከላ መልካዓምድር ውጤቶች ናቸው፡፡ በዓሉን የቱሪዝም ሚኒስትር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ከውሃ እና መስኖ ሚኒስተር ጋር ቅንጅታዊ ሆኖ ይከበራል፡፡ ግዮን በሰከላ ከውሃነት ያለፈ እንደ ጠበል (የተባረከ ውሃም -holy water) ስለሚታይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ ጥር 13 በዓባይ ምንጭ የአቡነ ዘራቡሩክ መታሰቢያ በዓል ይከበራል፡፡ ከየሀገሪቱ ማዕዘን ከ200 ሺ ህዝብ በላይ በጥር ሰሞን ግሽ ዓባይን እንደሚጎበኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply