በሙስና የተማረረው አንድ ግብፃዊ ታሂር አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ

በሙስና የተማረረው አንድ ግብፃዊ ታሂር አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ግብፃዊ ግለሰብ ታሂር አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት ማቃጠሉ ተነገረ።

እራሱን በእሳት ያቃጠለው ግለሰብ አሁን ላይ በካይሮ በሚገኝ ሆስፒታል የህምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ነው ሬውተርስ በዘገባው ያሰፈረው።

ክስተቱን በተመለከተ እስከአሁን ድረስ ከመንግስት ባለስልጣናት የተሰጠ አስተያየት የለም።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የተዘዋወረ ተንቀሳቃሽ ምስል እራሱን በእሳት ያያዘው ግለሰብ በሀገሪቱ ባለው ሙስና መማረሩን ሲግልፅ ነበረ ተብሏል።

ግለሰቡ እራሱን በእሳት ከማቃጠሉ በፊት ከፍ ያለ ድምፅ እያሰማ ያልቅስ እንደነበርም ዘገባው አስፍሯል።

 

The post በሙስና የተማረረው አንድ ግብፃዊ ታሂር አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply