በሚቀጥለው በጀት አመት በሻይና በሩዝ መስክ ላይ በስፋት ይሰራል…ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ

በመገባደድ ላይ ባለው በጀት አመት በሩዝ ምርት ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል።

ይህም በአሃዝ ሲነፃፀር ባለፉት አመታት ዘጠኝ ሚሊዬን ኩንታል የሩዝ ምርት በዘንድሮ አመት ወደ 37 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ማምረት ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይ በበጀት አመት በዚህ አመት የተገኘውን አመርቂ ውጤት በእጥፍ እናሳድገዋለን ብለዋል።

በተጨማሪም

የፋይናስ ሴክተሩ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ ጤናማ ነው ተባለ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ደ/ር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በዚሁ ጊዜ ታዲያ በሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ የፋይናስ ሴክተር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ ጤናማ ነው ብለዋል።

ለዚህም ምክንያቱ የሀገር ውስጥ ባንኮች መስፋፋት እና ማደግን ተከትሎ መሆኑ ተነስቷል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ፣የፋይናንስ ዘርፉ ባንኮች ዛሬ ላይ ከ17 ወደ 32 ደርሰዋል ብለዋል።

ወደ 38 ሚሊዮን የነበረው የቁጠባ ደብተር ደግሞ ከ100 ሚሊዮን በላይ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህም የሚያሳየው የፋይናንሻል ዘርፉ ጤናማና መሻሻል እንደሚታይበትና ባንኮች ትርፋማም መሆናቸውን ጠቋሚ ነው ብለዋል።

በልዑል ወልዴ

ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply