በሚቺጋን ሦስት ተማሪዎች ተገደሉ ስድስት ቆሰሉ

https://gdb.voanews.com/51F2DDF0-1A06-4B9D-AE6A-77BC9369D7F5_cx0_cy15_cw0_w800_h450.jpg

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚችጋን ክፍለ ግዛት ከዲትሮይት ከተማ 48 ኪሌሜትር ርቆ ኦክላንድ ውስጥ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ውስጥ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነ የ15 ዓመት ወጣት በትናንትናው ዕለት በከፈተው ተኩስ ሦስት ተማሪዎችን ሲገድል ሌሎች ስድስት ተማሪዎችን ደግሞ ማቁሰሉ ተነገረ፡፡

ስሙ ያልተገለጸው ተጠርጣሪው ተማሪ፣ ምንም ጉዳት ያልደረሰበት ሲሆን፣ ከያዘው መሳሪያ ጭምር በቁጥጥር ስር መዋሉንና የድርጊቱም ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply