You are currently viewing በሚዥጋ ወረዳ ወሪንቃ ቀበሌ በርካታ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጆች በእርሻ ማሳቸው ላይ እያሉ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 12 ቀን 2014…

በሚዥጋ ወረዳ ወሪንቃ ቀበሌ በርካታ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጆች በእርሻ ማሳቸው ላይ እያሉ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 12 ቀን 2014…

በሚዥጋ ወረዳ ወሪንቃ ቀበሌ በርካታ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጆች በእርሻ ማሳቸው ላይ እያሉ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በቤጉ ክልል ከማሼ ዞን ሚዥጋ ወረዳ ወሪንቃ ቀበሌ 4ኛ ጎጥ በርካታ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጆች በእርሻ ማሳቸው ላይ እያሉ በጉምዝ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። እገታው የተፈጸመው ጥቅምት 10 ቀን 2014 በጠራራ ጸሀይ በማሳቸው ላይ እንዳሉ ሲሆን ቁጥራቸው ቢያንስ ከ7 በላይ እንደሚሆን ተገልጧል። ከ40 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ሚሊሾችና ሌሎች የጸጥታ አካላት ወደ ጫካ በማቅናት አሰሳ ቢሄዱም ሊያገኟቸው አልቻሉም። ይህ የጉምዝ አማጺ ቡድን ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመተባበር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን በተለይ ንጹሃን አማራዎችን፣ በርታዎችንና ሌሎችንም መጨፍጨፍ ከጀመረና መደበኛ ስራው ካደረገው ከራርሟል። እየሞተ ያለው አማራ እንዳይደራጅ፣ እንዳይታጠቅና የመኖር መብቱን እንዳያስከብርም በመንግስት መዋቅር በእጅጉ የተገፋና እንዲሞት የተፈረደበት በመሆኑ በከፍተኛ ፈተና ላይ ነው ሲሉ ምንጮች በተደጋጋሚ ይናገራሉ። ቡድኑ በኢምፑቺያ (ዲዲጋ) እና ሀሮ ደዴዳ ቀበሌዎች የነበሩ በርካቶችን በመግደል፣ ሽህዎችን በማፈናቀል ተቆጣጥሮ የማሰልጠኛ ካምፕ ማድረጉ ይታወቃል። ዳሩ ግን የህዝቡን እልቂት በየጊዜው ያለመከላከል የሚቆጥረው የመከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው መስተዳድር ካምፓቸውን በቅርብ እርቀት እየተመለከተ አልታዘዝኩም በሚል እርምጃ ለመውሰድ አለመፍቀዱ ነው ይላሉ። የተገደሉ፣ የቆሰሉና የታገቱ ወገኖችን ለማስመለስ ሲጠየቁ ፍቃደኛ አይደሉም ሲሉ ይወቅሳሉ። እንደአብነት ሶጌ ከተማ ውስጥ ያለው የመከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ኃይል፣ በወሪንቃ ቀበሌ ፏፏቴ ከተማ ላይ ያለው ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የንጹሃንን ህይወት ካልታደገ ምን ይሰራልናል ሲሉም ጠይቀዋል። ትብብር የነፈጉንም ከመንግስት አካላት መካከል ይህን አማጺ ኃይል የስልጣን ማስጠበቂያ አድርጎ የሚጠቀምበት አካል ስላለ ነው ብለው ይደመድማሉ። አሚማ ስለጉዳዩ ለማነጋገር በሚል ወደ ቤጉ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ አሻድሌ ሀሰን በእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም የሚጠራ ስልካቸውን አላነሱም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply