በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች መበራከት የመንግስት ኃላፊዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተባለ::በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚስተዋሉት ግጭት ቀስቃሽና ሀሰተኛ መረጃዎች መበራከት፣…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/WXI9YUVYLJEghsHF1cYb6LsV6Gu7DBNglTn7cSnBjoKiWveVVx9pmADkKtECH9uV3J2cZ8oFU30N_-d7ZtCJs6K8VQW99qHcwXRZu4nsA3aZf5YwLKj62PEMu1g1RVqPK5UyJeKWmvqzd5jbuB4XwrYo1iXPEVTHitDLSg6bmRUPHzvKjWk-u2egXB2LaZthO5g7Ugwb1rCcz6oue-IofXpz5ty8RfR1FCSprvZIwrUt3zMbORv1zUUk3vb9YBzhewMAsPhFNJ1buB9IgGrXBemELi7q2S8t_nUkQBbKEDDZzHu5PKy8ELHYIaPYNf4buwowcNZcMWi_s4FllUSH4A.jpg

በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች መበራከት የመንግስት ኃላፊዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተባለ::

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚስተዋሉት ግጭት ቀስቃሽና ሀሰተኛ መረጃዎች መበራከት፣ የዲጂታል ሚዲያ አረዳድ ክህሎት ያላቸው የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የመብቶችና ዲሞክራሲ እድገት ማዕከል ካርድ አስታውቋል።

የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የዲጂታል ሚዲያ አረዳድ ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ከየትኛውም ወገን የሚሰራጩ መረጃዎችን መርምረው እንዲጠቀሙ ያስችላል ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የዲጂታል ሚዲያ አረዳድ ክህሎት ወይንም ዲጂታል ሚዲያ ሊትረሲ አረዳድ ገና መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፣ በዚህ ላይ እንደ ሀገር ብዙ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የመንግስት ባለስልጣናትና ታዋቂ ግለሰቦች ጭምር የሚያስተላልፏቸውን መልዕክቶች እንዲሁም መረጃዎች መርምሮ የሚወስድ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባም አንስተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴኮኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በበኩላቸው፣ ማህበራዊ ሚዲያን ለሰላም እንጅ ለጥፋት ምንጭነት ማዋል አይገባም ብለዋል።

ለዚህም የዲጂታል ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ለማስተማርና ለማብቃት እንደ ሀገር ብዙ ስራ ይጠበቃል ባይ ናቸው፡፡
የሜታ ኩባንያም በኢትዮጵያ የዲጂታል ሚዲያ አረዳድ ክህሎትን ለማሳደግ እንደሚሰራ በምስራቅ አፍሪካ የኩባንያው የህዝብ ፖሊስ ዳይሬክተር መርሲ ኒዴግዋ አስታውቀዋል።

በአባቱ መረቀ

ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.c

Source: Link to the Post

Leave a Reply