በማህበራዊ ሚዲያ በንቃት በመሳተፍና ሀሳቡን ፊት ለፊት በመግለጽ የሚታወቀው ወጣት ምስጋናው በለጠ ማንነታቸው ባልታወቁ ሲቪል የለበሱ አካላት ድብደባ እና የአፈና ሙከራ ተደረገበት። አማራ ሚዲ…

በማህበራዊ ሚዲያ በንቃት በመሳተፍና ሀሳቡን ፊት ለፊት በመግለጽ የሚታወቀው ወጣት ምስጋናው በለጠ ማንነታቸው ባልታወቁ ሲቪል የለበሱ አካላት ድብደባ እና የአፈና ሙከራ ተደረገበት። አማራ ሚዲ…

በማህበራዊ ሚዲያ በንቃት በመሳተፍና ሀሳቡን ፊት ለፊት በመግለጽ የሚታወቀው ወጣት ምስጋናው በለጠ ማንነታቸው ባልታወቁ ሲቪል የለበሱ አካላት ድብደባ እና የአፈና ሙከራ ተደረገበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማህበራዊ ሚዲያ በንቃት በመሳተፍና ሀሳቡን ፊት ለፊት በመግለጽ የሚታወቀው ወጣት ምስጋናው በለጠ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ”ምስጋናው ዘ ግዮን” ግንቦት 8 ቀን 2013 ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሲቪል የለበሱ አካላት ድብደባና የአፈና ሙከራ እንደተደረገበት ገልጧል። ከቀናት በፊት በሚቀርበው ሰው በኩል “አካሄድህን ብታስተካክል ይሻልሃል፤ በኋላ ማንም አያስጥልህም” የሚል ይዘት ያለው ማስጠንቀቂያ ነገር ደርሶት እንደነበር አውስቷል። የአማራ ብልጽግና አካሄድ የመዳኛችን መንገድ ነው ብዬ አላምንም ምክንያቱም የማባበል ፖለቲካ ስለሆነ ነው የሚለው ምስጋናው በዚህ አቋሙ ደስተኛ ያልሆኑ አካላት ለማሳፈን ሞክረዋል ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል። ለተፈናቃዮች በመድረስ የሚታወቀው ምስጋናው በባህር ዳር ከተማ መኖሪያ ቤቱ ሊገባ ትንሽ ሲቀረው ነው ሶስት ሰዎች መኪና ይዘው በመምጣት እንፈልግሃለን ሲሉ መጀመሪያ ላይ በጨዋ ደንብ የጠየቁት። ወደኋላ ግን ነገሩ እየከረረ ሲመጣ፣ አንደኛው “ምን ያስፈራሃል ? አንተ የህግ ሰው አይደለህም?” ለተባለው “የህግ ነገር ካነሳችሁማ ትዕዛዝ አምጡ” ማለቱን አውስቷል። በመሃል አንደኛው የመኪናውን በር ከፍቶ በመምጣት በኃይል ታቅፎ ለማስገባት እንደታገለው፣ ሁለተኛው ደግሞ እግሩን ሲመታው የአካባቢው ሰው ከቦ እንዳስጣለው ተናግሯል። የአፋኞቹ መኪና የፊት መስታወት በወጣቶች እንደተሰበረባቸው የገለፀው ምስጋናው መንገድ እየተዘገባቸው መሆኑንና አፍነው መውሰድ እንደማይችሉ በማወቃቸው ዐይኔ ላይ በቦክስ በመምታት ጉዳት አድርሰውብኛል፤ ምንአልባትም በቀለበት እንደተመታሁ ይሰማኛል ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply