በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የአልኮል መጠጦችን ማስታወቂያ ለመቆጣጠር አዲስ አሰራር ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የአልኮል መጠጦችን ማስታ…

በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የአልኮል መጠጦችን ማስታወቂያ ለመቆጣጠር አዲስ አሰራር ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡

የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የአልኮል መጠጦችን ማስታወቂያ ለመቆጣጠር አዲስ አሰራር ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ እንደተናገሩት የአልኮል መጠጦች በማህበራዊ ሚዲያ እንዴት መተዋወቅ እንዳለባቸው የሚወስን አዲሰ አሰራር እየዘረጋን ነው ብለዋል፡፡

አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግም ከመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ጋር በጋራ እንደሚሰሩም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የምግብ እና የመድሀኒት አዋጅ ቁጥር 1112 አንቀፅ 74 (4) መሰረት የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) እና በቢልቦርድ አማካኝነት ማስተዋወቅን የሚከለክለው ዕገዳ በ2011 ዓ.ም ተግበራዊ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ማንኛውም የብሮድካስት ሚዲያ የአልኮል መጠጦችን ማስታወቂያ ማስተላለፍ እንዳቆሙ ይታወቃል፡፡

በሐመረ ፍሬዉ

ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply