በማሊ በታጣቂዎች የታገቱት የማሊ ፖለቲከኛና የፈረንሳይ የእርዳታ ሰጭ ሰራተኛ ተለቀቁ

በማሊ በታጣቂዎች የታገቱት የማሊ ፖለቲከኛና የፈረንሳይ የእርዳታ ሰጭ ሰራተኛ ተለቀቁ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በማሊ በፅንፈኛ ታጣቂዎች ታግተው የቆዩት የማሊ ፖለቲከኛና ፈረንሳዊት የእርዳታ ሰጭ ሰራተኛ መለቀቃቸው ተሰምቷል።

ሶፊ ፔትሮኒን የተባሉት የ 75 ዓመቷ የእርዳታ ሰጭ ሰራተኛ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ከሚነገርላቸው ታጣቂዎች መለቀቃቸውን ለቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ ከፈረንሳይ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ አለመኖሩ ነው የተገለጸው።

የእርዳታ ሰጭ ሰራተኛዋ የታገቱት በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ጋኦ ከተማ ለስራ በሄዱበት ወቅት መሆኑ ተነግሯል።

ሶፊ ፔትሮኒን በፈረንጆቹ 2016 ነበር የታገቱት።

በተመሳሳይ ሁኔታ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ የታገቱት የ70 ዓመቱ ተቃዋሚ እና የቀድሞ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ሶማይላ ሲሴን ታጣቂዎች መልቀቃቸው ተገልጿል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post በማሊ በታጣቂዎች የታገቱት የማሊ ፖለቲከኛና የፈረንሳይ የእርዳታ ሰጭ ሰራተኛ ተለቀቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply