በማሊ አዉቶብስ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ በማእከላዊ ማሊ በአንድ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸዉንና 53 የሚደርሱ…

በማሊ አዉቶብስ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

በማእከላዊ ማሊ በአንድ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ከ10 ሰዎች በላይ መሞታቸዉንና 53 የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸዉን የሆስፒታል ምንጮች አመልክተዋል፡፡
ፍንዳታዉ ባንዲጋራ እና ጎንዳካ በተሰኙ ቦታዎች መካከል መከሰቱ ታዉቋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማሊ ታጣቂ ሃይሎች እየተዘዋወሩ ጥቃት እየፈጸሙባት እንደሆነ እየተነገረ ነዉ፡፡
ማሊ ከአስርት አመታት በላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤታቸዉን ያፈናቀሉ የታጠቁ አማጺ ቡድኖች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በመታገል ላይ ናት፡፡

በማሊ የሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንዳመለከተዉ፣ እ.ኤ.አ በ 2022፣ 72 ሰዎች በፈንጅዎች መገደላቸዉን አረጋግጧል፡፡
አብዛኛዎቹ ተጎጅዎችም ወታደሮች መሆናቸዉን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply