በማዕከላዊ ሶማልያ 219ሺሕ ሰዎች በጎርፍ ተፈናቀሉ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-42da-08db540d3621_w800_h450.jpg

በማዕከላዊ ሶማልያ በለደወይን ከተማ፣ የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ አካባቢውን በማጥለቅለቁ፣ 219ሺሕ ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ ጎርፉ እና የወንዝ ሙላቱ በአጠቃላይ 460ሺሕ ሰዎችን ለችግር መዳረጉ ተነግሯል፡፡

እንደ አሶሺዬትድ ፕረስ ዘገባ ከኾነ፣ ጎርፉ በበለደወይን ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ቢሮዎችን ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲዘጉ አስገድዷል።

የጎርፍ አደጋው፣ በታሪክ በአካባቢው ያልታየ መኾኑን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በመናገር ላይ ናቸው።

በለደወይን የተሰኘችው ከተማ፣ በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንደሚኖርባት ተመልክቷል።

የጎርፉ አደጋ የተከሠተው፣ በተከታታይ ዓመታት ድርቅ ምክንያት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶማልያውያን፣ ለረኀብ በተጋለጡበትና አገሪቱ ከእስላማዊ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋራ በመዋጋት ላይ ባለችበት ወቅት ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply