በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ከተማ አንድ የፋኖ አደራጅ መምህር መታሰሩ መምራንና ተማሪዎችን አስቆጣ፤ የማሰሮ ደንብ ሀይስኩል የትምህርት መርኃ ግብር ተስተጓጉሎ መዋሉም ተሰምቷል። አማራ…

በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ከተማ አንድ የፋኖ አደራጅ መምህር መታሰሩ መምራንና ተማሪዎችን አስቆጣ፤ የማሰሮ ደንብ ሀይስኩል የትምህርት መርኃ ግብር ተስተጓጉሎ መዋሉም ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ከተማ አንድ የፋኖ አደራጅ መምህር መታሰሩ መምራንና ተማሪዎችን ማስቆጣቱን የገለጹ የአሚማ ምንጮች እንደሚሉት የማሰሮ ደንብ ሀይስኩል የትምህርት ሂደትም ተስተጓጉሎ መዋሉን ተናግረዋል። አብራራው መንግስቴ የተባለ የማሰሮ ደንብ መምህር መጋቢት 28/2014 ፋኖን በማደራጀቱና በፋኖነቱ መታሰሩ ተገልጧል። የመምህሩ መታሰር አግባብ አይደለም ያሉ የማሰሮ ደንብ ሀይስኩል መምህራንና ተማሪዎች የትምህርት ጊዜ እንዲስተጓጎል በማድረግ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል ተብሏል። በመሆኑም መምህራንና ተማሪዎች የተፈጸመውን እስር በመቃወም ለጥያቄያቸው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ስለመሆኑ ምንጮች ለአሚማ ተናግረዋል። ፋኖ መምህር አብራራው መንግስቴ በእነ አንተነህ ድረስ የሚመራው የምኒልክ ብርጌድ አባል በመሆን በማሰሮ ደንብ ከተማ በቸገረ ጊዜ ለህዝብ እና ለሀገር መከታ የሚሆኑ የፋኖ አባላትን ስለማደራጀቱም ተነግሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ስለተከሰተው ሁኔታ ያነጋገራቸው የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ የፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኢ/ር እዘዘው አቸነፈ በበኩላቸው መምህር አብራራው መንግስቴ ወደ ፊዛራ በመሄድ ወጣቶችን ጫካ ላይ ሰብስቧል፤ ጥይትም እንዲተኮስ አድርጓል በሚል ተጠርጥሮ ነው ብለዋል። ፋኖነትን የምንደግፈው እና የምናበረታታው ጉዳይ ነው በመሆኑም አደረጃጀቱ ግልጽ እንዲሆን እንዲሁም ከአካባቢያችን የጸጥታ ስጋት አኳያ ጥይት ተኩስና በጫካ ወጣቶችን መሰብሰብ እንዲቆም እንፈልጋለን ብለዋል። ከዛ ውጭ ግን የፋኖ አደረጃጀትን የምንደግፈው በመሆኑ ፋኖ በመሆኑ አናስርም፤ አሁንም ጉዳዩ ተጣርቶ መምህሩ ይፈታል ሲሉ ተናግረዋል። በማሰሮ ደንብ እና አካባቢው የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን ለማስተካከልም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንና የህዝብ ድጋፍም እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል። ፎቶ_የማዕከላዊ አርማጨጭሆ አብን

Source: Link to the Post

Leave a Reply