በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የእገታ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ በዞኑ…

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የእገታ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዞኑ…

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የእገታ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በዞኑ ጣቁሳ ወረዳ ሮቢት ቀበሌ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡30 አንደበት አዘነው የተባለውን ተከሳሽ ለጊዜው በቁጥጥር ስር ካልዋለው ግብር አበሩ ጋር በመሆን መንገድ ዘግቶ በተሸከርካሪ ይጓዙ ከነበሩ ሶስት ግለሰቦች መካከል አንዱን በማገት እንድ ሚሊዮን ብር ጥይቋል፡፡ አጋቹ ግለሰብ በድርድር ሁለት መቶ ሽህ ብር ከታጋቹ ቤተሰቦች ከተቀበ በኋላ የታገተውን ግለሰብ ለቀውታል። ይህ መረጃ የደረሰው የጣቁሳ ወረዳ ፖሊስም ባደረገው ክትትል ወንጀል የፈፀመውን እንደበት አዘነውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለጣቁሳ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ልኳል፡፡ መዝገቡን የተመለከተው የጣቁሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ አንደበት አዛነውን በ14 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የዘገባው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዋና ክፍል ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply