
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ነዋሪዎች ብልጽግና ደግፉኝ ብሎ የጠራውን ሰልፍ ወደ ተቃውሞ ቀይሮታል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 10/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ነዋሪዎች ለብልጽግና ድጋፍ የተጠራውን ሰልፍ ቀይረው የኦህዴድ ብልጽግና ብልሹ ስርዓቱን በመቃወም እና ጀግናውን የአማራ ፋኖን በመደገፍ ሰልፍ አካሂደዋል። በሰልፍ የፋኖን እና የአማራን ህዝብ ትግል እንዲሁም የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ መፎክሮች ተሰምተዋል። ከመፈክሮች መካከል ጥቂቶቹ፦ የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ቀይ መስመራችን ነዉ!! ፋኖ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነዉ!! የአማራ ህዝብ ሁሉም ፋኖ ነዉ !! ብልጽግና የአንድ ብሄር ፓርቲ ነው !! የታሰሩ ልዮሀይሎች፣ፋኖዎች፣ምሁራኖችና ጋዜጠኞችን ይፈቱ!! ያለ አግባብ ግድያ ና እስራት ይቁም!! ብሄርን ያተኮረ ግድያ ይቁም!! አንድነት ሀይል ነው! ለዘገባው_የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደርን በምንጭነት ተጠቅመናል።
Source: Link to the Post