You are currently viewing በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ በአንድ የአብን ታዛቢ፣ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ደግሞ በሁለት የመኢአድ አመራሮች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሟል፤ በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ደግ…

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ በአንድ የአብን ታዛቢ፣ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ደግሞ በሁለት የመኢአድ አመራሮች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሟል፤ በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ደግ…

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ በአንድ የአብን ታዛቢ፣ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ደግሞ በሁለት የመኢአድ አመራሮች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሟል፤ በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ደግሞ በእናት ፓርቲ የወረዳው አስተባባሪ መኖሪያ ቤት ላይ ጥይት ሲተኮስ ማደሩን ፓርቲው አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ በሚሊሻዎችና ስምሪት ላይ በነበሩ የልዩ ኃይል አባላት አማካኝነት በመኖሪያ ቤቴ ከበባ ተደርጎ በፈፀሙብኝ ከፍተኛ ድብደባ በእጄ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል ያለው የአብን ታዛቢ ሱራፌል ነጋ ነው፡፡ ሱራፌል ነጋ ለአሚማ እንደገለፀው ድብደባው የተፈፀመው ሰኔ 13 ቀን 2013 የአብን አንድ የመቀስቀሻ ወረቀት ከኪስህ ተገኝቷል በሚል ነው። በአካሌ ላይ በዱላ ከፍተኛ ድብደባ ከፈፀሙ በኋላ ጥለውኝ ተመልሰዋል ያለው ሱራፍኤል ከአሁን ቀደም እንደተመረቅሁ የብልጽግና አባል ሁን በማለት በተደጋጋሚ ሲጠይቁኝ ባለመፍቀዴ ደስተኞች አልነበሩም ብሏል። በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ የእናት ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ገብረ ማርያም ስመኘው በመኖሪያ ቤት ከምሽቱ 5:15 ላይ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ፓርቲው አስታውቋል። በእስቴ 3 ምርጫ ጣቢያ ላይ ፓርቲው በብዙ ችግር ውስጥ አልፎ የተሻለ ድምፅ ማምጣቱን ተከትሎ ገዥው ፓርቲ መቀበል አልችልም ማለቱንና ሂደቱን በአስተውሎት ይከታተሉ እንደነበር ተገልጧል። አቶ ገብረ ማርያም ጉዳዩን ለወረዳው የጸጥታ አካላት እና ለሚመለከተው አካል እልባት እንዲሰጠው ያስታወቁ ሲሆን የፓርቲው ዋና ጽ/ቤትም ለችግሩ አስቸኳይ እልባት እንዲሰጠው ለምርጫ ቦርድ እና ለፍትህ ተቋማት ማሰወቁን ተገልጧል። በተያያዘ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ከምርጫው ጋር ተያይዞ በአመራሮቹና በአባላቱ ላይ በብልጽግና ካድሪዎችና በፀጥታ አካላት አማካኝነት የተፈፀመውን በደል ለአሚማ ገልጧል። በተለይም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ በመቶ አለቃ መምህር መላኩ መዳልቾ እና በአምሳ አለቃ ጴጥሮስ ዲንጋሞ በብልጽግና ካድሪዎች፣በደህንነት እና በፀጥታ አካላት ትናንት ሰኔ 16 ቀን 2013 የተፈፀመውን የድብደባ ሙከራ በማህበረሰቡ ትብብር መክሸፉ ተነግሯል። መቶ አለቃ መምህር መላኩ መዳልቾ እና አምሳ አለቃ ጴጥሮስ ዲንጋሞ ከአሚማ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምርጫው ያለ ታዛቢ በአፈና የተደረገ በመሆኑ ታአማኒነትና ዲሞክራሲያዊነት የጎደለው ነው፤ በመሆኑም ውጤቱ እንዲሰረዝ በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ብሎም ለማስቀረት ታስቦ የተፈፀመ ድብደባና ወከባ ነው ብለውታል። ፎቶው_ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ የአብን ታዛቢ_ሱራፌል ነጋ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply