በማይካድራ ሕወሓት በንፁሀን አማራዎች ላይ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በፍጥነት ፣ በጥልቀት ፣ በገለልተኝነት እና በብቃት ተመርምሮ ተጠያቂዎች በሕግ ፊት ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው አ…

በማይካድራ ሕወሓት በንፁሀን አማራዎች ላይ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በፍጥነት ፣ በጥልቀት ፣ በገለልተኝነት እና በብቃት ተመርምሮ ተጠያቂዎች በሕግ ፊት ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው አምኒስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማይካድራ በጅምላ ጭፍጨፋ የተገደሉ በርካታ ዜጎች መሞታቸውን የሚያሳዩ ምርመራዎችን ማረጋገጡን አምኒስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይ-ካድራ በኖቬምበር 9 ቀን ምሽት ላይ በርካታ እና ምናልባትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጩቤ ተወግተው ወይም ታንቀው ስለመገደላቸው ማረጋገጡን በሪፖርቱ ገልጧል፡፡ የድርጅቱ የቀውስ ማስረጃ ቤተ-ሙከራ በከተማው ውስጥ ተበትነው ከተጣሉበት ላይ አስከሬኖች ሲወሰዱ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን እና ቪዲዮዎችን በዲጂታል መልኩ መያዙን አረጋግጧል፡፡ በማይካድራ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍምስሎቹም የቅርብ ጊዜ መሆናቸውን የሳተላይት ምስሎችንም ጭምር በመጠቀም ማረጋገጡን ጠቁሟል። እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ጥቃት በምንም መንገድ የማይሳተፉ የቀን ሠራተኞች ሆነው በሚታዩ እጅግ በጣም ብዙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ ጭፍጨፋ ስለመሆኑም አምኒስቲ ጠቅሷል፡፡ የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ዲሮሴ ሙቼና እንዳሉት ይህ በትግራይ ውስጥ ያለው የግንኙነት መረብ እንደተዘጋ ከተፈፀሙት መጠኑ ብቻ የሚነገርለት አስከፊ አደጋ ነው ብለዋል፡፡ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚካሄደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተጠያቂነት እና የግልጽነት ተግባርን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉንም ግንኙነቶች ክፍት እንዲያደርግ እንዲሁም ሰብአዊ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተቆጣጣሪዎች ያለገደብ ተደራሽነትን ማረጋገጥ አለባቸው ብሏል አምኒስቲ በመግለጫው፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጦርነቱ ውስጥ ባሉ ሁሉም ወገኖች የሚፈጸሙ ጥሰቶችን ለመዘገብ እና ለማጋለጥ ሁሉንም መንገዶች መጠቀሙን እንደሚቀጥልም ገልጧል፡፡ ከቀናት በፊት በማይካድራ አስከፊው ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ወዲያውኑ ከተማዋን ለጎበኙት የመከላከያ ሰራዊት ምግብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ሲያቀርቡ የነበሩ ድርጅቱ ምስክሮችንና ከአደጋው በህይወት የተረፉ የአይን እማኞችን በማነጋገር ማረጋገጡን ነው ያስታወቀው። አብዛኞቹ አስከሬኖች የተገኙትም በማይካድራ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቅራቢያ በሚገኘው ቶው ኤን ማእከል እና ወደ አጎራባች ሁመራ ከተማ በሚወስደው መንገድ ላይ መሆኑን ምስክሮቹ እና የተረጋገጡ ምስሎች ገልጸዋል ብሏል፡፡ ሬሳዎችን ያዩ ሰዎች ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለጹት ቢላዋ እና ማጭድ በመሳሰሉ ሹል መሳሪያዎች የተጎዱ የሚመስሉ ቁስሎች ክፍተቶች እንዳሏቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባሰራቸው ገለልተኛ የስነ-ህክምና ባለሙያ አረጋግጧል ብሏል፡፡ ምስክሮቹ እንዳሉት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ከሟቾች መካከል የተወሰኑ ቁስለኞችን አግኝተው በአብርሃ ጅራ እና በጎንደር አቅራቢያ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች ስለመውሰዳቸው ገልጧል። “የቆሰሉት በሜንጫ ፣ በመጥረቢያ እና በቢላዎች እንደተጠቁ ነግረውኛል፡፡ በተጨማሪም የሞቱት ሰዎች በሹል ነገሮች እንደተጠቁ ከቁስሎቹ መለየት ይችላሉ፡፡ በጣም ዘግናኝ ነው እናም በሕይወቴ ውስጥ ይህን በመመልከቴ በእውነት አዝናለሁ ”ሲል አንድ የተረበሸ ምስክር ተናግሯልም ብሏል አምኒስቲ በመግለጫው፡፡ በደም የተጠመቀው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለግድያው ተጠያቂው ማን እንደሆነ እስካሁን ማረጋገጥ አልቻለም ነገር ግን አምኒስቲ ያነጋገራቸው ምስክሮች ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሃት) ታማኝ የሆኑ ኃይሎች ለጅምላ ግድያው ተጠያቂ እንደሆኑ ስለመናገራቸው ጠቅሶ ሶስት ሰዎች ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለጹት ከእልቂቱ የተረፉት በትግራይ ልዩ ፖሊስ አባላት እና በሌሎች የህወሃት አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል ነው ያለው፡፡ “ወደ ከተማው ስንገባ ያየነው አውዳሚ ነበር፡፡ መንገዶቹ በተለይም በከተማው መሃል ላይ በአስከሬኖች ተዘርዘዋል፤ ከተማዋን ወደ ሁመራ በሚያገናኘው መንገድ ላይ፡፡” ሲሉ አንድ የአይን ምስክር ስለመናገራቸው አስታውቋል። ዲፕሮሴ ሙቼና “የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ይህንን ግልፅ ጥቃት በፍጥነት ፣ በጥልቀት ፣ በገለልተኝነት እና በብቃት መመርመር እና ተጠያቂዎችን በሕግ ፊት ለፍርድ ማቅረብ አለባቸው” ብለዋል፡፡ “ሆን ተብሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በፍፁም የተከለከሉ እና የጦር ወንጀሎች መሆናቸውን” ግልፅ ማድረግ መደረግ እንዳለበት ያስታወቁት ዲፕሮሴ ሙቼና በትግራይ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች በድርጊታቸው ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕጎች እና ለሰብዓዊ መብት ሕጎች ሙሉ አክብሮት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡ ማይካድራ ውስጥ በይፋ የሟቾች ቁጥር እስካሁን ባይታወቅም በአማራ ክልል መንግስት የሚዲያ ወኪል አብመድ ወደ 500 የሚጠጉ ተጎጂዎች እንዳሉ የገለጸ ሲሆን በዋናነት አማራዎች የጥቃቱ ሰለባ ስለመሆናቸው አስታውቋል። አስክሬኖቹን ከጎዳናዎች ለማፅዳት እየረዳ ያለው አንድ ግለሰብ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለጸው በመንግስት የተሰጠ የአንዳንድ ተጎጂዎችን መታወቂያ ካርዶች ተመልክተናል እና አብዛኛዎቹ አማራዎች ስለመሆናቸው ተናግሯል ብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) እንደዘገበው ባለፉት ውስን ቀናት ብቻ 7000 የሚጠጉ ስደተኞች ከሁመራ፣ማይካድራና አካባቢው ሸሽተው ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል ስለማለቱ ተጠቅሷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply