በማይካድራ ምድር ያልተፈጸመ ኢ-ሰባዊ ድርጊት የለም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ                 አሻራ ሚዲያ          ታህሳስ፡-07/…

በማይካድራ ምድር ያልተፈጸመ ኢ-ሰባዊ ድርጊት የለም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-07/…

በማይካድራ ምድር ያልተፈጸመ ኢ-ሰባዊ ድርጊት የለም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-07/4/13/ዓ.ም ባህርዳር በማይካድራ ምድር ያልተፈጸመ ኢ-ሰባዊ ድርጊት የለም ሲሉ ከቦታው የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውሰዋል፡፡ በወልቃይት ጠገዴ ፣ ዳንሻ ፣ ባዕከርን ፣ ሁመራ ፣ ማይካድራ እና ሌሎች አካባቢ ትህነግ በአማራ ህዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ ገና ተዳሶና ተነግሮ አለማለቁን ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። በተለይም በማይካድራ ምድር የተፈጸመው ድርጊት ለማመን ያስቸግራል። ያማልም። ማይካድራ ላይ ያልተፈጸመ ኢ-ሰባዊ ድርጊት የለም። በዓለም ላይ ያልተፈጸሙ ሁሉም ኢ-ሰባዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል ብለዋል ምንጫችን። በተጠቀሱት አካባቢዎች የአማራ ህዝብ በጅምላ ተገሎ በጅምላ መቀበር ብቻ ሰይሆን ህጻናት በቋንቋቸው እንዳይማሩ ግፍና በደል ተፈጽሞባቸዋል ፣ እናቶች ወልደው እንዳይስሙ ዘር አምክን እንክብል እንዲወስዱ መደረጋቸውን አውስተዋል። እንደምንጫችን ገለጻ ሰው የሆነ ሁሉ በወልቃይት ጠገዴና ሌሎች አካባቢ አ በአማራ ህዝብ ላይ በትህነግ አማካኝነት የደረሰበትን በደልና እንግልት ከሞት በተረፉ አማራዎች መካከል ቁሞ መስማት ትህነግ አውሬ እንጂ ሰው እንዳልነበረ ማረጋገጥ እንዳለበት ነው የተናገሩት። በአሁኑ ስዓት ደግሞ በመተከልና በወለጋ ከማይካድራው ጋር ተመሳሳይ ድርጊት ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ጭፍጨፋ እየተካሄደ መገኘቱን ገልጸው መንግስት ይህንን ተግባር በይፋ አለማውገዙ የከፋ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ምንጫችን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በመተከልና በወለጋ ለሚካሄደው የዘር ጭፍጨፋ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ግንባር ቀደም ተዋኒያን በመሆናቸው መንግስት ለህግ ማቅረብና ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም በመተከልና በወለጋ የሚደረገውን ዘርን የማጥፋት ጥቃትና አጥፊዎችን መንግስት በችልተኝነት መመልከቱን ምንጫችን ኮንነዋል፡፡ በመጨረሻም መንግስት በአካባቢው ከሞት የተረፉ የአማራ ተወላጆች ህይወታቸውን ለመታደግ ትኩረቱን ሁሉ መተከልናወለጋ ላይ ማድረግ አለበት ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply