
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በማይካድራ ለበርካታ ንጹሓን ዜጎች ሞት እና ንብረት መውደም ወንጀል ተሳትፎ አላቸው በተባሉ 21 ተጠርጣሪዎች ላይ የተጀመረው ምስክር የመስማት ሂደት ዛሬም ቀጥሏል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ላይ ማስረጃ ለማቆየት አቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት መዝገብ መክፈቱ ይታወቃል፡፡
ይህንን ተከትሎም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍድር ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የአቃቤ ህግ ትላንት ካቀረባቸው 11 ምስክሮች ውስጥ ሦስቱን አሰምቷል፡፡
ቀሪዎቹን ደግሞ በዛሬው ዕለት እያሰማ ይገኛል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
The post በማይካድራ በተፈጸመው ወንጀል ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የተጀመረው ምስክር የመስማት ሂደት ዛሬም ቀጥሏል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post