በማይካድራ ተጨማሪ 74 ሰዎች ተገድለው ተገኙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማይካድራ ከተማ አብነት እና ሴንትራል መውጫ በተባሉ ገጠራማ…

በማይካድራ ተጨማሪ 74 ሰዎች ተገድለው ተገኙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማይካድራ ከተማ አብነት እና ሴንትራል መውጫ በተባሉ ገጠራማ ቦታዎች በሕወሓት ጨፍጫፊ ቡድን ተጨማሪ 74 ሰዎች ተገድለው ተገኝተዋል። 56 ዜጎች በአንድ ሥፍራ የተገኙ ሲሆን፣ አስከሬናቸው የውኃ ጉድጓድ ውስጥ የተከተተ ሰለባዎች መኖራቸውም ተረጋግጧል። ሕወሓት ከጅምላ ግድያው በኋላ የዘር ማጥፋቱን ወንጀል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለመደበቅ የግድያውን ሰለባዎች ከከተማዋ አርቆ መደበቁን ከጥቃቱ የተረፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሕወሓት ከጭፍጨፋው በተጨማሪም በከተማዋ የሚኖሩ አማራዎች በስጋት እንዲሸሹ የማድረግ ትልም እንደነበረውም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መረጃ ጨፍጫፊው ሕወሓት በትንሹ 600 ሰዎች እንደገደለ እና በየቦታው የተገደሉ ሰዎች ስለሚገኙ ቁጥሩ ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል። በገዳይ ቡድኑ ሕይወታቸው ያለፈ ንጹሐን ዜጎች አስከሬን በክብር እንዲያርፍ ስለመደረጉም የአብመድ ዘገባ አመልክቷል። ከሀዲው ህወሀት ፀረ አማራ ማኒፌስቶ በማዘጋጀት ላለፉት በርካታ ዓመታት የለይቶ ዘርበማጥፋት ወንጀል ሲፈፅምና ሲያስፈፅም መኖሩ ይታወቃል። ከሰሞኑም ሳምሪ የተባለ ገዳይ ቡድን በማዘጋጀት ማይካድራ ላይ በንፁሀን አማራ ላይ የፈፀመው አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት የጭካኔውንና የተስፋ ቆራጭነቱን ጥግ ያሳያል የሚሉ በርካቶች ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply