በማይካድራ እና በቃፍታ ሁመራ ንፁሀን አማራዎችን በአሰቃቂ መልኩ በጅምላ ጨፍጨፈው ወደ ሱዳን የሸሹ ሕወሓት ያሰማራቸው ነፍሰ ገዳዮች ለሕግ እንዲቀርቡ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በማይካድራ እና በቃፍታ ሁመራ ንፁሀን አማራዎችን በአሰቃቂ መልኩ በጅምላ ጨፍጨፈው ወደ ሱዳን የሸሹ ሕወሓት ያሰማራቸው ነፍሰ ገዳዮች ለሕግ እንዲቀርቡ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በማይካድራ እና በቃፍታ ሁመራ ንፁሀን አማራዎችን በአሰቃቂ መልኩ በጅምላ ጨፍጨፈው ወደ ሱዳን የሸሹ ሕወሓት ያሰማራቸው ነፍሰ ገዳዮች ለሕግ እንዲቀርቡ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስቴ ታደገ ንጉሴ ይባላል። በወልቃይት ጠገዴ የሁመራ ነዋሪ ሲሆን ወልቃይት፣ጠገዴና ራያ በታሪክ የአማራ እንጅ የማንም ሆነው እንደማያውቁ ይታወቃል ይለናል። መንግስቴ ታደገ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ከሆኑት ታጋዮች ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልጾ ዛሬ ላይም ከወልቃይት ጠገዴ እስከ ሁመራ የሕግ ማስከበር ስራ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከልም በሁመራ ያለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ምን ይመስላል የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት ጠይቋል። መንግስቴ ታደገ ሕወሓት ለረዥም ጊዜ የወልቃይት፣ጠገዴና ራያ አማራዎችን በጅምላ ሲገድል፣ሲቀብር፣ሲያስርና ሲያፈናቅል እንደነበር አውስቷል። በተለይም ሕወሓት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎም ከአማራ የፀጥታ አካላትና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ሕግ በማስከበር ረገድ የራሱን አሻራ ማሳረፉን ተናግሯል። በማይካድራና በቃፍታ ሁመራ በዘር አጥፊው የሕወሓት ቡድን የተፈፀመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አሰቃቂነት የገለፀው መንግስቴ አየር ማረፊያ የተባለ አካባቢን ጨምሮ በሌሎችም ብዙ መቃብር እየተገኘ ነው፤ እያረደ ወደ ወንዝ የጣላቸውም ብዙ ናቸው ይለናል። ይኑሩ አይኑሩ መዳረሻቸው ያልታወቀ ወይም የሟች አስከሬን ያልተገኘላቸው የማይካድራና የሁመራ ቤተሰቦችም የደም እምባ እያነቡ በስቃይ ላይ ስለመሆናቸው አስታውቋል። አማራ የበቀል ስሜት ስለሌለው እንጅ በከሃዲው ሕወሓት የተፈፀመው ጭፍጨፋ ዘግናኝና አብሮ ለመኖር እንኳ የማያስችል እንደነበር ጠቅሶ ወገኖቻችን በአሰቃቂ መልኩ በገጀራ አርደው ወደ ሱዳን የሸሹ ሕወሓት ያሰማራቸው ነፍሰ ገዳዮች በሕግ እንዲጠየቁ ሲል መንግስትን አሳስቧል። የሕወሓት ዋነኛ ምሽግ መቀሌ በመከላከያ ሰራዊት መያዙን ተከትሎም በርካታ የአሸባሪው ቡድን ተዋጊዎች ዩኒፎርማቸውን በመቀየርና መሳሪያቸውን በመደበቅ ወደ ሱዳን ለመሻገር በሁመራ በኩል ሲመጡ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ስለመሆኑም አስታውቋል። እነ ታጋይ ጎይቶም እርስቃይ፣ ሀይሌ ማሞ፣ፀሀየ አታላይና ሌሎችን በርካታ ጀግኖች መስዋዕት በማድረግ አካባቢውንና ህዝቡን ከጨቋኙ ቡድን ነጻ ማድረግ መቻሉን ያወሳው መንግስቴ ማንነትና እርስታችን ለማስመለስ በእርግጥም ብዙዎች ለመሰዋት ዝግጁ ነበርን ሲልም አክሏል። የሁመራ ነዋሪዎች ተረጋግተው ወደ መደበኛ ኑሮአቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ያለው መንግስቴ ሕወሓት በፎቅ ላይ በመሆን አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በማለት በህዝቡ ላይ መተኮሱን አውስቶ በዚህም የሸሹ በርካታ ወገኖች ዛሬ ላይ እየተመለሱ ወንጀለኞችን አጋልጠው እየሰጡ፣የመቃብር ስፍራ እያሳዩና በአጠቃላይ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር እየተባበሩ ስለመሆኑ ነው የተናገረው። ከሁመራ ነዋሪ ታጋይ መንግስቴ ታደገ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply