በማይካድራ የተፈጸመውን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል በልዩ የአቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት ማየት እንደሚገባ የህግ ምሁራን ተናገሩ፡፡              አሻራ ሚዲያ…

በማይካድራ የተፈጸመውን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል በልዩ የአቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት ማየት እንደሚገባ የህግ ምሁራን ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

በማይካድራ የተፈጸመውን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል በልዩ የአቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት ማየት እንደሚገባ የህግ ምሁራን ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-16/03/13/ዓ.ም በማይካድራ የተፈጸመው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል በልዩ የአቃቤ ህግ ጽሕፈት ቤት እና ችሎት ተቋቁሞ ጉዳዩ ሊታይ እንደሚገባ ሙህራን ተናገሩ፡፡ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው የመጀመሪያ የምርመራ ውጤት የጨፍጫፊው ትህነግ ልዩ ኃይል እና ሌሎች ኢ-መደበኛ የሆኑ ቡድኖች እንደተሳተፉበት ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ የትህነግ ቡድን በባለፉት ዓመታትም በጉራፈርዳ፣ በወለጋ፣ በመተከል እና በሌሎችም አካባቢዎች ብሔርንና ማንነትን መሰረት አደርጎ የዘር ጭፍጨፋ ፈፅሟል፤ በተመሳሳይ የማይካድራው የዘር ጭፍጨፋ በአወደ ውጊያ ውስጥ የተፈፀመ የጦር ወንጀል ነው ብለዋል፡፡ በጦርነት ውስጥ የንጹኃንን ደህንነት መጠበቅ እንደሚገባ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1949 የፈረመችው የጄኔቫ ኮንቬንሽን ስምምነት ያስቀምጣል፡፡ ሆኖም ጨፍጫፊው ትህነግ ንጹሃንን ዒላማ አታድርግ የሚለውን አለም ዓህግተላልፏል ሲሉ የህግ ምሁሩ ደጀኔ የማነህ ተናግረዋል፡፡ የተፈፀመውን ወንጀል ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የጭፍጨፋውን ቡድን ድርጊት የሚመረምር የአቃቤ ህግ አደረጃጀት ያስፈልጋል ም ብለዋል፡፡ መንግስት ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ እያካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የህግ ምሁሩ ደጀኔ አስገንዝበዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply