‹በማይካድራ ጭፍጨፋ 1100 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ተገደው ተደፍረዋል› ኢሰመጉ አማራ ሚዲያ ማዕከል  ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም           አዲስ አበባ ሸዋ  ኢሰመጉ በመግለጫው…

‹በማይካድራ ጭፍጨፋ 1100 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ተገደው ተደፍረዋል› ኢሰመጉ አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢሰመጉ በመግለጫው…

‹በማይካድራ ጭፍጨፋ 1100 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ተገደው ተደፍረዋል› ኢሰመጉ አማራ ሚዲያ ማዕከል ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢሰመጉ በመግለጫው የተፈጠረው ሁኔታ በምንም ዓይነት ሁኔታ ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን ደህንነትና የሲቪል ንብረቶችን አደጋ ውስጥ የሚከት እንዳይሆን ሲወተውት ቆይቷል ያለ ሲሆን ሆኖም፤ በወቅቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂ ግድያዎችና ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ ለልዩ ልዩ አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶች እንዲሁም ከፍተኛ ለሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰለባ ሆነዋል ሲል ታህሳስ 16 ባወጣው መግለጫ አትቷል። ኢሰመጉ፤ ሁኔታውን ለማጣራት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያ ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥፍራው በመላክ በወቅቱ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምንነት የመለየት ሥራ ከህዳር 24 – ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በማይካድራ፣ ሁመራ፣ አብደራፊ፣ አብርሀጅራ፣ ዳንሻ እና ጎንደር ከተሞች ተዘዋውሮ የመስክ ምርመራ ሥራ አከናውኗል፡፡ በምርመራውም የሚከተሉትን ግኝቶች አስፍሯል። በጥናቱም በአብዛኛው ተጠቂ የነበሩት የሰሊጥ ና ማሽላ እርሻዎችን ተከትሎ የቀን ስራ የሚሰሩ ሰራተኞች መሆናቸው ተገልጧል:: ከጥቃቱ ሁለት ቀናት በፊት ቤት ለቤት ፍተሻ በማይካድራ ፖሊስ ና የትግራይ ልዩ ሀይል የተደረገ ሲሆን ስጋት የገባቸው ወደ አማራ ክልል ለመግባት ፈልገው መውጣት ሳይችሉ ቀርተዋል:: ጥቃት የተፈፀመ እለት የፖሊስ እና የልዩ ሀይል አባላት እንዲሁም ሳምሪ ከሚባል ሰፈር የመጡ የትግራይ ወጣቶች ማንም ሰው ከቤት እንዳይወጣ ትእዛዝ ሰጥተዋል::የአማራ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩበት ‹ግምብ ሰፈር› የትግራይ ተወላጅ የሆኑ እና ያልሆኑትን በመለየት ጥቃት አድርሰዋል:: ጥቃቱ በአብዛሃኛው በድምፅ አልባ መሳሪያ ተፍፅሟል:: ጭፍጨፋው በግልፅ ብሄርን መስረት ያደረገ እና በአብዛኛው አማራ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የኢሰመጉ ጥናት አመልክቷል:: በጭፍጨፋው የሞቱ ሰዎችን ለመቅበር 4 ተከታታይ ቀናት ወስዷል ያለው ኢሰመጉ 86 ጉድጓድ ውስጥ ከ5-6 ሰዎችን በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ተቀብረዋል ብሏል: ከዚህ በተጨማሪም ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ውጭ በቅርብ ርቀት ላይ 42 ሰዎች ፣ ስለላ መስመር 57 ሰዎች፣ ወልደአብ መስመር 56 ሰዎች፣ ቀበሌ 04 ድልድይ 6 ሰዎች በአቅራቢያው ካለ የጎርፍ ድልድይ 18 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብር መኖራቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል:: በፍለጋው አሁንም ድረስ አስክሬናቸው ያልተገኙና ያልተቀበሩ መኖራቸውን የኢሰመጉ ባለሙያዎች አረጋግጠዋል:: በአንዳንድ አካባቢ ቦታው ሞቃታማ በመሆኑ አስክሬን ለማንሳት ስላስቸገረ እዚያው ተቀብረዋል:: የምርመራ ቡድኑ ከማይካድራ በተጨማሪም በዳንሻ እና በሁመራ ከተሞች ተመሳሳይ ጭፍጨፋ መፈፀሙን አረጋግጧል:: በሁመራ ስድስት እንዲሁም በዳንሻ ሁለት ታዳጊዎች ተገድለዋል:: በጭፍጨፋው 1100 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ተገደው ተደፍረዋል:: ተጎጅዎች ከጥቃቱ በሗላ ምንም አይነት አካላዊም ይሁን ስነልቦናዊ የህክምና ድጋፍ አላገኙም:: ጥቃት እንዳይደርስባቸው የተከላከሉ የሸሸጉ እና መረጃ በመስጠት እንዲሸሹ በማድረግ የሰብዓዊ ተግባር የሰጡ የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውን የኢሰመጉ መግለጫ አመላክቷል::

Source: Link to the Post

Leave a Reply