በማጀቴ ከተማ የሰፈረው እና ምሽግ በመስራት በከባድ መሳሪያ ተኩ ስ ከፍቶ የሰነበተው ጦር አዛዥ መምህራንን በመ ሰብሰብ ትምህርት እንዲያስጀምሩ ያደረጉት ማግባባት አልተሳካም ተብሏል፤ መምህራ…

በማጀቴ ከተማ የሰፈረው እና ምሽግ በመስራት በከባድ መሳሪያ ተኩ ስ ከፍቶ የሰነበተው ጦር አዛዥ መምህራንን በመ ሰብሰብ ትምህርት እንዲያስጀምሩ ያደረጉት ማግባባት አልተሳካም ተብሏል፤ መምህራንም የሰላም ዋስትና በሌለበት ትምህርት ተጀምሯል በማለት ተማሪዎችን ለማስመጣት ይከብደናል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 4/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በማጀቴ ከተማ የሰፈረው እና ምሽግ በመስራት በከባድ መሳሪያ ተኩ ስ ከፍቶ የሰነበተው እነ አብይ አህመድ ያሰማሩት ጦር ሚያዝያ 23/2015 ፋኖ አለ በሚል በከባድ መሳሪያ በከፈተው ተኩስ ሁለት ገበሬዎች መገደላቸው፣ አንዲት እናት ደግሞ ተኩሱን ተከትሎ በጃራ ወንዝ ሙላት መወሰዷ ይታወቃል። አሁን ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነዋሪ “ትጥቄን አስረክቤ በኦነጋዊያን ከእነ ቤተሰቦቼ አልገደልም” በሚል በጫካ ባለበት ሁኔታ ከሰሞኑ የጦሩ አዛዥ አስር ራሱን በጦር መሳሪያ ታጅቦ ት/ቤት በመግባት መምህራንን ሰብስቦ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማግባባት ሞክሯል። ይሁን እንጅ ምንም ዓይነት የሰላም ዋስትና በሌለበት ትምህርት ተከፍቷል በሚል ተማሪዎችን ለማስመጣት ይከብደናል የሚል ምላሽ ስለመስጠታቸው የማጀቴ ምንጮች ለአሚማ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply