በሜክስኮ ድንበር የሚመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ሂደት የሚያሳጥር አሰራር ወጣ

https://gdb.voanews.com/092b0000-0a00-0242-1cbb-08d9ebdced13_cx0_cy6_cw0_w800_h450.jpg

የባይደን አስተዳደር በሜክሲኮ ድንበር በኩል የሚመጡ የጥገኝነት (አሳይለም) ጠያቂዎችን አቤቱታ ለመወሰን ዓመታት የፈጀውን ጊዜ ቢያንስ በወራት ለማሳጠር የሚረዳ የአሰራር ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ፡፡

አዲሱ ደንብ የኤምግሬሽን ሰራተኞች በሜክሲኮ በድንበር በኩል የሚመጡትን የጥገኘት ጥያቄዎችን የኤምግሬሽን ዳኞች መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው እዚያ ቶሎ በማየት የሚያጸድቁበትን ወይም ውድቅ የሚያደርጉበት ሥልጣን ሊሰጣቸው እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

የኤምግሬግሽን ፍርድ ቤቶች ወደ 1.7 ሚሊዮን በሚጠጉ አመልካቾች ውዝፍ ፋይል የተጨናነቁ መሆናቸው ሲነገር አሁን ባለው አሰራር አንድን የጥገኘነት ጉዳይ ተመልክቶ ለመወሰን በአማካይ እስከ አራት ዓመት ጊዜ የሚወስድባቸው መሆኑን ተነገሯል፡፡

አዲሱ ደንብ በሁለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply