You are currently viewing #በምሥራቅ ጎጃም አርሶ አደሮች በማዳበሪያ ዋጋ ንረት ላይ ቅሬታ አቀረቡ ባህርዳር:- መጋቢት 13/2014 ዓ.ም                 አሻራ ሚዲያ #Ethiopia  | በምሥራቅ ጎጃም ዞን…

#በምሥራቅ ጎጃም አርሶ አደሮች በማዳበሪያ ዋጋ ንረት ላይ ቅሬታ አቀረቡ ባህርዳር:- መጋቢት 13/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ #Ethiopia | በምሥራቅ ጎጃም ዞን…

#በምሥራቅ ጎጃም አርሶ አደሮች በማዳበሪያ ዋጋ ንረት ላይ ቅሬታ አቀረቡ ባህርዳር:- መጋቢት 13/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ #Ethiopia | በምሥራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ከየወረዳው የተውጣጡ አርሶ አደሮች የወቅቱን የማዳበሪያ አቅርቦትና ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪን በተመለከተ የተሰማቸውን ቅሬታ ለሚመለከታቸው የዞን አመራሮች አቅርበዋል ። እንደ አርሶ አደሮች ገለፃ ለምርት መቀነስ ዋነኛ ምክንያት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል ማዳበርያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ሳይደርስ ከቀረና በዋጋው መናር ምክንያትም አርሶ አደሩ ገዝቶ መጠቀም ሳይችል ሲቀር እንደሆነ ይታወቃል ፤ ስለሆነም ለቀጣዩ የእርሻ ወቅት ማዳበሪያ በወቅቱና በበቂ መጠን ማቅረብ ካልተቻለ በምርት መቀነስም ሆነ በቀጣይ የአርሶ አደሩ ህይወት ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ከወዲሁ በአቅርቦትም ሆነ በዋጋ ጭማሪ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መንግስት በፍጥነት እንዲያስተካክል የሚሉ ጥያቄዎችን በጋራ ተሰባስበው ለዞን አመራሮች በማቅረብና ይህን የሚከታተል ኮሚቴ ከየወረዳው በመምረጥ ውይይታቸውን አጠናቀው በሰላም ተመልሰዋል። ምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply