በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ኢዴፓ የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተንዛዛ አሰራር ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ        አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ23/2…

በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ኢዴፓ የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተንዛዛ አሰራር ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ23/2…

በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ኢዴፓ የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተንዛዛ አሰራር ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ23/2013 ዓ.ም ባህር ዳር የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ እንዳስታወቀው ለዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የያዝነው ፕሮግራም ተሰርዟል ብሏል። ፓርቲው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላለፈብንን የስረዛ ውሳኔ አስመልክቶ ለዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቶ ነበር። መግለጫ ሊሰጡበት በታሰበው ሆቴሉ አካባቢው ያለው የካራማራ ፓሊስ ጣቢያ ፈቃድ አምጡ አለን እዛ ሄድን እነሱ ደግሞ ለቦሌ ክ/ከተማ ፓሊስ መምሪያ ላኩን እነሱ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ልከውን ነበር። ኮሚሽነሩን አናገርናቸው። እሳቸው ደግሞ ከንቲባ ፅ/ቤት ሄዳችሁ የሰላማዊና ህዝባዊ ስብሰባ ፈቃድ ክፍል ፈቃድ አምጡ አሉን ብሏል ፓርቲው። እኛም ሰልፍም አይደለም፣ ስብሰባም አይደለም ጋዜጣዊ መግለጫ ነው የምንሰጠው። ከዚህ በፊትም ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ስንፈልግ ይሄን ተጠይቀን አናውቅም። አሁን ምን የተለየ ነገር ተገኝቶ ነው አልናቸው። እሳቸውም ብዙ ነገር ተለውጧል። አዳዲስ ፕሮቶኮሎችም ወጥተዋል ብለው ለነገ እንደማንችል አሳውቀውናል ብሏል። እስካሁንም ያለውን ሂደት የተጓዝነው እየጠየቁን ያለው ተገቢ ጥያቄ ሆኖ ሳይሆን ማስጨረስ ስለነበረብን ነው። በመጨረሻ ያረጋገጥነው ግን ምን ያህል ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አደጋ ውስጥ መውደቁን ነው ብሏል ፓርቲው። ባለው የተጣበበ ሰዓት እና ሁኔታ ምንም ማድረግ ስለማንችል መግለጫው የተሰረዘ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን ብሏል ፓርቲው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply