
በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የዶኒ አቡነ ገ/መንፍስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ተፈጸመ። ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በቀን 29/10/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 5፡30 ጀምሮ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቦስት ወረዳ የዶኒ አቡነ ገ/መንፍስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ላይ የታጠቁ የኦህዴድ/ኦነግ ሀይሎች ጥቃት መፈጸማቸውን የአካባቢው ማህበረሰብ ገልጸዋል። በዚህም ጥቃት ቤተክርስትያን ውስጥ ሁለት ቦንብ የወረወሩ ስሆን አንዱ ፈንድቶ በቤተክርስቲያኑ ላይ ጉዳይ አድርሷል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ካህናትን ጨምሮ አራት(4) ሰዎች በታጠቁት ኃይሎች መወሰዳቸውንም ተናግረዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post