You are currently viewing በምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሽ መልካሳ በዶሮ እርባታ ማዕከል የሚገኙ ከ330 በላይ ተፈናቃይ አማራዎች ስልካቸውን እንደተቀሙ መሆኑ ተገለጸ፤ ከአፈና ለመሸሽ ሲሉ አንዳንዶች “ከመንግስት ምንም ነገር…

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሽ መልካሳ በዶሮ እርባታ ማዕከል የሚገኙ ከ330 በላይ ተፈናቃይ አማራዎች ስልካቸውን እንደተቀሙ መሆኑ ተገለጸ፤ ከአፈና ለመሸሽ ሲሉ አንዳንዶች “ከመንግስት ምንም ነገር…

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሽ መልካሳ በዶሮ እርባታ ማዕከል የሚገኙ ከ330 በላይ ተፈናቃይ አማራዎች ስልካቸውን እንደተቀሙ መሆኑ ተገለጸ፤ ከአፈና ለመሸሽ ሲሉ አንዳንዶች “ከመንግስት ምንም ነገር አልፈልግም” በሚል ፈርመው እንዲወጡ መደረጉ ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሆሮ ጉድሩ ዞን አቢደንጎሮ ወረዳ ተፈናቅለው ሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግላቸውና መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቂርቆስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ነበር። በ24 ሰዓት ከግቢ ለቀው እንዲወጡ እና ወደ አሩሲ ዞን አቦምሳ ወረዳ መርቲ ከተማ አዋሽ ጎለጎታ ቢደርሱም ተቀባይነት በማጣታቸው የካቲት 7 ቀን 2014 ወደ አዲስ አበባ የካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል። ይሁን እንጅ ከየካ ሚካኤል ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን፣ወደ ጃንሜዳ፣ወደ ደብረ ብርሃን፣ በመቀጠልም ወደ አሩሲ መርቲ በኃይል ተጭነው ቢወሰዱም በድጋሜ ተቀባይነት በማጣታቸው ወደ ምስራቅ ሸዋ ናዝሬት ዙሪያ አዋሽ መልካሳ በሌሊት ተገደው ተወስደዋል። ወደ ምስራቅ ሸዋ ናዝሬት ዙሪያ አዋሽ መልካሳ በኃይል የተወሰዱት 338 የሚሆኑ ተፈናቃይ አማራዎች በዶሮ እርባታ ማዕከል እንዲያርፉ መደረጋቸው እና ስልካቸውን በሙሉ በአካባቢው የመስተዳድር አካላት መነጠቃቸው ይታወቃል። አሚማ ያነጋገራቸው ምንጮች እንደነገሩት ተፈናቃዮቹ አሁንም ድረስ የእጅ ስልካቸውን እንደተነጠቁ ናቸው። ከተጠለሉበት አካባቢ ወጥተው የመንቀሳቀስ መብታቸው የተጣሰ ሲሆን በዙሪያው የፖሊስ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ለማወቅ ተችሏል። ከአካባቢው እንወጣለን ለሚሉት “ከመንግስት ምንም ነገር አልፈልግም” በሚል እየፈረሙ መውጣት እንደሚችሉ ተገልጧል። በዚህ መልኩ ፈርመው እንዲወጡ የተደረጉ አማራዎች ስለመኖራቸውና ሾልኮ የወጣም እንዳለ አሚማ ለማወቅ ችሏል። ማቆሚያ ያጣው፣ ለከት የለሹ ግፍ በጫካ እና በመሀል ከተማ ጭምር ተመሳሳይ አላማ እና ግብ ባላቸው ሁለት አካላት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገልጧል። ያለአንዳች ፋታ እየተፈጸመባቸው ያለው ድርብርብ በደል እንዲቆምላቸው የጠየቁት ተጎጅዎቹ ምንም እንኳን መጠነኛ የሆነ የምግብ አቅርቦት እየደረሳቸው ቢሆንም መውጫና መግቢያ የተነፈጋቸው መሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply