You are currently viewing በምስራቅ አማራ ፋኖ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ቤተሰቦች እና ጀግና ቁስለኞች በሙሉ:-    እንደሚታወቀው የትግራይ ወራሪ ሀይል በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ እና በሃገር ላይ በፈጸመው…

በምስራቅ አማራ ፋኖ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ቤተሰቦች እና ጀግና ቁስለኞች በሙሉ:- እንደሚታወቀው የትግራይ ወራሪ ሀይል በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ እና በሃገር ላይ በፈጸመው…

በምስራቅ አማራ ፋኖ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ቤተሰቦች እና ጀግና ቁስለኞች በሙሉ:- እንደሚታወቀው የትግራይ ወራሪ ሀይል በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ እና በሃገር ላይ በፈጸመው ክህደት እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንድሁም የአማራ እና የአፋር ህዝብን የህልውና አደጋ ለመጣል ባደረገው ወረራ እንደ ህዝብ በተደረገው አገር የማዳን የክተት ዘመቻ የምስራቅ አማራ ፋኖ ከራሱ ትጥቅና ስንቅ ባሻገር ከዉጭና ከሃገር ዉስጥ ከአማራ ህዝብ በሚያገኘው ድጋፍ ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሀገራዊ ግደታውን መወጣቱ ይታወቃል፡፡ ወደፊትም ሃገራዊ ግዴታውን ይወጣል። በዚህ ሃገር የማዳንና የማስቀጠል ትግል የህይወት መስዋዕትነት እና የአካል መስዋዕትነት ከፍለናል፡፡ ወደፊትም ለህዝብና ለሃገር እንደ አባቶቻችን መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ ነን፡፡ …ለከፈልነው መስዋዕትነትም ክብርና ኩራት ይሰማናል። ስለሆነም መስዋዕትነት የከፈሉ ጓዶቻችን ቤተሰቦች እንዲሁም ከባድና ቀላል ቁስለኛ ጓዶቻችን የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልታችሁ ራያ ቆቦ ከተማ ለምስራቅ አማራ ፋኖ ገቢ እንድታደርጉልን እናሳስባለን፡፡ 1ኛ.የጀግና ሟች ቤተሰቦች ከአካባቢያችሁ የወረዳ ፍ/ቤት የሞግዚትነት ወይም የወራሽነት ማረጋገጫ ለምስራቅ አማራ ፋኖ በሚል የውሳኔ ደብዳቤ ለምስራቅ አማራ ፋኖ እንድታስገቡ! 2ኛ.የአካል ጉዳት ማለትም የመቁሰል አደጋ የደረሰባችሁ ጀግኖች የደረሰባችሁን የጉዳት መጠን የህክምና አገልግሎት ካገኛችሁበት ሆስፒታል ለምስራቅ አማራ ፋኖ ማምጣት እንድትችሉ ደብዳቤ መጥታችሁ እንድትወስዱ! * ይህንን መረጃ የደረሳችሁ ሀገር ወዳዶች ለጀግና ሟች ቤተሰቦች እና ለጀግና ቁስለኞቻችን በመደወል መረጃውን በማድረስ እንድትተባበሩን ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። መረጃውን እስከ 15/07/2015 ማስገባት ይቻላል። ለበለጠ መረጃ:-0909099228 0900219912 0924499649 “ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው”

Source: Link to the Post

Leave a Reply