በምስራቅ አፍሪካ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ በቂ በጀት ባለመመደቡ ከፍተኛ ውድመት ሊያደርስ እንደሚችል የተበባሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አስጠነቀቀ፡፡

ከወራት በፊት በምስራቅ አፍሪካ አብዛኞቹ ሐገራት የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ፋኦ አስታውሷል፡፡ መንጋው መጥፋቱ ከተበሰረ ከወራት በኋላ ሰሞኑን በሐገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያና ሶማሊያ መታየቱ ተሰምቷል፡፡ በኮሮና ቫይረስና ጎርፍ የተጎዳው ዞኑ በአንድ ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ በዚሁ አደገኛ መንጋ መጠቃቱን ፋኦ አስታውቋል፡፡

የፋኦ ጥናት ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከሆነ መንጋው በኢትዮጵያና ሶማሊያ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ነው፡፡ ኬንያን እና ታንዛኒያን ጨምሮ በ11 ሐገራት ተሰራጭቶ የአርሶ አደሮችን ሕይወት አጣብቂኝ ውስጥ መክተቱን የድርጅቱ ሪፖርት ጠቁሟል፡፡

የሰሞኑ መንጋ በአንድ ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የተከሰተ መሆኑን የገለጸው ፋኦ በሶስቱ ዙሮች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ውድመት ማድረሱንም ነው የጠቆመው፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ሐገራት ለዚህ አደገኛ መንጋ ትኩረት ሰጥተው እስከ 38 ሚሊዮን ዶላር በጅተው ካልተከላከሉ በስተቀር በሰብል ላይ የሚያደርሰው ውድመት የከፋ ሊሆን እንደሚችል ፋኦ ማስጠንቀቁን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

****************************************************************************

ቀን 19/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post በምስራቅ አፍሪካ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ በቂ በጀት ባለመመደቡ ከፍተኛ ውድመት ሊያደርስ እንደሚችል የተበባሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አስጠነቀቀ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply