በምስራቅ ኬንያ በአል-ሻባብ በተፈፀመ ጥቃት አንድ ፖሊስ እና ሌላ ሲቪል ተገደሉ

https://gdb.voanews.com/2e4cb3e9-f245-45f3-911a-599c3e5a4989_w800_h450.jpg

በምሥራቅ ኬንያ ከሶማሊያ ጋር በምትዋሰነው ጋሪሳ በተባለች ስፍራ ትናንት ለተገደሉት አንድ የፖሊስ አባልና አንድ ሲቪል ተጠያቂው አል-ሻባብ ነው ሲል የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል። 

የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ አህመድ ሁሴን ከስፍራው እንደዘገበው ስድስት ሰዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው የፖሊስ መኪና የተቀበረ ፈንጂ ላይ ሲወጣ ሁለቱ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ተናግረዋል።

አዛዡ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ እንደነገሩት የተጎዱ ሌሎች ሶስት ሰዎች በሄሊኮፕተር ወደ መዲናዋ ናይሮቢ ለህክምና ተወስደዋል። 

ከጥቃቱ ጀርባ አል-ሻባብ እንዳለና አንድ የጸጥታ ቡድንም የቡድኑን ተዋጊዎች በማሰስ ላይ መሆናቸው አዛዡ ገልፀዋል። 

የትናንቱ ጥቃቱ የመጣው በአል-ሻባብ ሳይፈጸም አይቀርም በተባለ ሌላ ጥቃት በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የሚገኝ የሬዲዮ መገናኛ አንቴና ከጥቂት ቀናት በፊት ከወደመ በኋላ ነው። 

ኬንያ ከአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር የሚያገለግል ሰራዊት ወደ ሶማሊያ ከላከች ጀምሮ፣ መሠረቱን በሶማሊያ ያደረገው አል-ሻባብ በኬንያ ላለፉት 10 ዓመታት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply