በምስራቅ ወለጋ ሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርቲ ወረዳ የሚገኙ አማራዎች ጭፍጨፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለጹ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// ነዋሪዎቹ ለአሻራ ሚዲያ እንደ…

በምስራቅ ወለጋ ሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርቲ ወረዳ የሚገኙ አማራዎች ጭፍጨፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለጹ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 7/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// ነዋሪዎቹ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለጹት ከትናንት ጀምሮ በአካባቢው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ገብተው መትረጊስና ሌላ ከባድ መሳሪያ በመጠቀም ከባድ ጥቃት እየፈጸሙ እንደሆነ ገልጸውልናል፡፡ በጥቃቱም እስካሁን በውል ያልተለዩ ንጹሀን አማራዎች ሲገደሉ የቀንድ ከብቶቻችንን ጨምሮ የሀብት ንብረት ዘረፋና የቤት ማቃጠል ተግባር እየፈጸሙ እንደሚገኙ በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 06/2013 ዓም በስልክ ነግረውናል ፡፡ ነዋሪዎቹ ዛሬ ጥቅምት 07/2013 ዓም ደግሞ እንደገለጹልን በአካባቢው የመንግስት የጸጥታ ሀይል የሰላም ማስከበር ስራ እየሰራ እንዳልሆነ ገልጸው ብዙ ቁጥር ያላቸው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እንዳሉ እና የአካባቢውን የኦሮሞ ማህበረሰብ በማስተባበር የሀብት ንብረት ዘረፋ እየፈጸሙ ነው ብለዋል፡፡ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ ግለሰቦችም የቅርብ ወገኖቻችንና የምናውቃቸው ሲሆኑ እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ ለማወቅ አልቻልንም ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮቻችን ከነዋሪዎች ጋር ያደረግነው የስልክ ቆይታ ከአሻራ ሚዲያ ዩቲዩብ ቻናል ያገኙታል እንድትከታተሉት እንጋብዛለን፡፡ በቴሌግራም ቻናላችንም ያገኙናል https://t.me/asharamedia24 https://youtu.be/Ia1Y4z8My80

Source: Link to the Post

Leave a Reply