በምስራቅ ወለጋ በጃርሲ ወረዳ የሚገኙ አማራዎች ከጥቅምት አራት ጀምሮ ማንም የመንግስት አካል አልደረሰልንም ሲሉ ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ። አሸዳራ ሚዲያ ህዳር 02…

በምስራቅ ወለጋ በጃርሲ ወረዳ የሚገኙ አማራዎች ከጥቅምት አራት ጀምሮ ማንም የመንግስት አካል አልደረሰልንም ሲሉ ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ። አሸዳራ ሚዲያ ህዳር 02 / 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በምስራቅ ወላጋ ጃርሲ ወራዳ የሚገኙ አማራዎች ከጥቅምት አራት 2013 ዓም ጀምሮ የኦነግ ታጣቂዎች በአካባቢው በሚገኙ አማራዎች ላይ የመግደል፤የማፈናቀልና የሀብት ንብረት ዘረፋ እያደረጉ እንደሚገኙ በአካካቢው የሚገኙመ አማራዎችን ምንጭ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ በጃርሲ ወረዳ የሚገኙ ምንጫችን ከቦታው እንዳረጋገጡልን በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ታጣቂ ቡደን ሀብት ንብረት በመዝረፍ ላይ ሲሆን ለመንግስት ብናሳውቅም ተገቢውን መፍትሄ አላገኘንም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት ቢሆንም በታጣቂ ቡድኑ እየተሳደድን በመሆኑ የደረሱ ሰብሎችን ለመሰብሰብ አልቻልንም ብለዋል፡፡ በጫካ የምንገኝ አማራዎችም አስከፊ ችግር ላይ ነን ያሉ ሲሆን ልጆቻቸው በጫካ ተጠልለው እየኖሩ እንደሆነ እና የጃርሲ ወረዳ ተስፋ ሰጭ መፍትሄ እየሰጠን አይደለም ብለውናል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply