You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትን ከተማ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በግፍ የታሰሩ ወገኖች አድራሻ አለመታወቁ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ፤ ቢያንስ አድራሻቸውን በትክክል አሳውቁን የሚል ጥሪ ለአፋኙ ክፍል…

በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትን ከተማ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በግፍ የታሰሩ ወገኖች አድራሻ አለመታወቁ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ፤ ቢያንስ አድራሻቸውን በትክክል አሳውቁን የሚል ጥሪ ለአፋኙ ክፍል…

በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትን ከተማ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በግፍ የታሰሩ ወገኖች አድራሻ አለመታወቁ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ፤ ቢያንስ አድራሻቸውን በትክክል አሳውቁን የሚል ጥሪ ለአፋኙ ክፍል ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መምህር ፈንታሁን አለምዬ ይባላል፤ ስራው አስተማሪነት ነው። ከሚኖርበት እና ከሚያስተምርበት አካባቢ በጸጥታው ችግር ምክንያት ተፈናቅሎ በአንገር ጉት ከተማ መኖር ጀምሮ ነበር። መምህር ፈንታሁን አለምዬ በመምህርነት ሙያው መስራት እየቻለ በግጭቱ ምክንያት ተፈናቅሎ ከሚኖርበት አከባቢና በሙያው መስራት ባይችልም ወደ ግብርና ስራ ለመሰማራት ተገዷል። በቆይታው ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ስለነበርም የእለት ጉርሱን ለቤተሰቦቹ ለማሟላት ሲል ከመምህርነት ወደገበሬነት እራሱን ቀይሮ በመንደር 4 ቀበሌ የእርሻ መሬት ገዝቶ በማረስ ለፍሬ አድርሶ ነበር። ሆኖም ግን በህዳር 24/2015 ጉትን ከተማ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት በአማራ ላይየፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በከተማዋ የሚገኙ አማራዎችን አፈሳ እየተፈጸመ መሆኑ ይታወቃል፤ ከ200 በላይ አማራዎች በአስከፊ እስር ላይ መሆናቸው ግልጽ ነው። መምህር ፈንታሁን ወደ እርሻ ቦታው አዝመራውን ለመሰብሰብ በመሔድ ላይ እያለ በኦሮሚያ ልዩ ሐይል ተይዞ ተወስዷል። ሁለት ልጆች ያሉት መምህር ፈንታሁን በአባታቸው ከቤት መጥፋት የተነሳ ልጆቹን ጨምሮ መላ ቤተሰቡ አድራሻው እንኳ ባለመታወቁ ተረብሸዋል። ልጆችም “እናታቸውን አባታችን የት ነው⁉ አባዬን አምጪ⁈” በማለት በጣፋጭ የህጻንነት አንደበት ወላጅ እናታቸውን እየጠየቁ ነው። በዚህም የተነሳ ልጆቹ “አባታችን ሳይመጣ በማለት ምግብም አንበላም‼” እያሉ እናታቸውን እያስቸገሩ ስለመሆኑ በቅርብ የሚያቋቸው ተናግረዋል። መምህር ፈንታሁን ከተወሰደ ከ17 ቀን በላይ ሲሆን እስካሁን ያለበትን ሁኔታ እንደማይታወቅ ተገልጧል። በመጨረሻም የመምህር ፈንታሁንን ጨምሮ በርካታ በአማራዊ ማንነታቸው ምክንያት ብቻ የታሠሩ ስላሉ ለቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ አሳሪው ክፍል እንዲያሳውቅ በማሳሰብ ጭምር አጉልዞ ጥያቄ መረጃውን አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply