You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ  ወለጋ ዞኖች ከህዳር 9 ጀምሮ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ በተፈጸመው ጥቃት 219 አማራዎች በግፍ ሲገደሉ፣ 107 ቆስለዋል፤ 40  የሚሆኑት ታግተው ደብዛቸው…

በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ከህዳር 9 ጀምሮ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ በተፈጸመው ጥቃት 219 አማራዎች በግፍ ሲገደሉ፣ 107 ቆስለዋል፤ 40 የሚሆኑት ታግተው ደብዛቸው…

በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ከህዳር 9 ጀምሮ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ በተፈጸመው ጥቃት 219 አማራዎች በግፍ ሲገደሉ፣ 107 ቆስለዋል፤ 40 የሚሆኑት ታግተው ደብዛቸው ስለመጥፋቱ የአማራ ማህበር በአሜሪካ በሪፖርቱ አመላካተ። ታሕሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ማህበር በአሜሪካ በምስራቅ ወለጋ ዞን እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች ከህዳር 9/2015 ጀምሮ እስከ ወሩ ፍጻሜ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ በኦነግ ሸኔ እና በአካባቢው ቄሮዎች በግፍ የተገደሉ አማራዎችን በዝርዝር አስታወቀ። በጥቃቱ ዙሪያ መረጃ ሲያሰባስብ መቆየቱን የገለጸው የአማራ ማህበር በአሜሪካ መጠነ ሰፊ የሆነ ማንነት ተኮር ጥቃት በወለጋ አማራዎች ላይ መፈጸሙን በሪፖርቱ አስታውቋል። ማህበሩ ከጥቃቱ ከተረፉት፣ ከተጎጅ ቤተሰቦች እና ከዐይን እማኞች ያሰባሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ ሪፖርት ማጠናቀሩን ጠቁሟል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ኦነግ ሸኔ እና የአካባቢው ጽንፈኛ ቄሮዎች በቅንጅት ግድያ፣ ዝርፊያ እና ማፈናቀሉን እንደፈጸሙት ገልጧል። የማህበሩ ሪፖርት እንዳመለከተው በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ባሉ ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አካባቢዎች:_ 1) 219 አማራዎች በግፍ ተገድለዋል፤ 107 ቆስለዋል፤ 40 የሚሆኑ አማራዎች ከኪረሞ እና ከሀሮ አዲስ ዓለም ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፤ እንደተገደሉ ይገመታል። 2) 62 የሚሆኑ አማራዎች በፌደራል እና በክልሉ የጸጥታ አካላት ቅንጅት በአንገር ጉትን ከተማ ከህግ ውጭ ለሆነ ዘፈቀዳዊ እስር ተዳርገዋል። 3) በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከሁለቱም ዞኖች መፈናቀላቸው ተገልጧል። 4) በብዙ መቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት የአማራ ንብረት ዝርፊያ፣ ውድመት እና ቃጠሎ የደረሰበት መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል። በአጠቃላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በማንነታቸው ብቻ ለግድያ እና ለጉዳት መዳረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ መፈናቀላቸውን በሪፖርቱ አመላክቷል። የአማራ ማህበር በአሜሪካ በሪፖርቱ እንደገለጸው በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በግፍ ከተገደሉት አማራዎች መካከል:_ 1) መሀመድ ከማል፣ 2) ከማል አሊ፣ 3) ኡመር አደም፣ 4) ኡመር መኮንን፣ 5) ኡስማን የሱፍ፣ 6) ንጉስ ዘውዱ፣ 7) ሰዋለች ሙሄ፣ 😎 መሀመድ ይመር፣ 9) መሀመድ ዳውድ፣ 10) መርከብ ተሰማ፣ 11) አብደላ አደም፣ 12) ሳኒ ከማል፣ 13) መሀመድ አሊ፣ 14) ኡመር አሊ፣ 15) ጀማል አደም፣ 16) ቃሲም ሲራጅ፣ 17) ጥላሁን ዘነበ፣ 18) ታጁ አህመድ፣ 19) ኡስማን ኢብራሂም፣ 20) አስካለ ደሳለኝ፣ 21) የሱፍ መሀመድ፣ 22) ተመስገን መልክነው፣ 23) እባቡ ይመር፣ 24) አስናቀው ካሳው፣ 25) ሀሰን ልዬው፣ 26) ሽርቴ ፈንታው፣ 27) ሰጤ ልዬው፣ 28) ተሾመ አበበ፣ 29) አህመድ ከማል፣ 30) ሁነኛ ደምሌ፣ 31) አንዳርጌ ሰቲያለው፣ 32) አበበ ውንጭቴ፣ 33) ማማር፣ 34) ዘመን ታደለ፣ 35) አስቻለ፣ 36) ክብረት አለኝ፣ 37) አሊ ሞገስ፣ 38) ከማል ፈድሉ፣ የ80 ዓመቱ አዛውንት አባ ከማል ፈድሉ ከ20 ቤተሰቦቻቸው ጋር ነው የተገደሉት። ባለቤታቸው፣ ልጆቻቸው፣ የልጅ ልጆቻቸው እና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተገድለዋል። 39) በቃሉ፣ 40) ኡስማን አሊ፣ 41) መሀመድ ይመር፣ 42) አብዱ አሊ፣ 43) ጀማል ይማም፣ 44) አለልኝ ደሳለኝ፣ 45) ካሴ መሀመድ፣ 46) ተመስገን መስጠት፣ 47) ደበበ እውነቴ፣ 48) እስሌማን ይመር፣ 49) ትዕግስት አታላይ፣ 50) እታትዬ አበራ፣ 51) ወንዱ፣ 52) መሀመድ ይብሬ፣ 53) መዲና ከማል፣ 54) ጦይባ ከማል፣ 55) ወርቂት መሀመድ፣ 56) አህመድ ቢላል፣ 57) ሀሰን ሙሀመድ፣ 58) የሻረግ እውነቱ፣ 59) ሁነኛው እውነቱ፣ 60) ኡመር ካሳው፣ 61) እባቡ ደሳለው፣ 62) ደመላሽ ተፈሪ፣ 63) መሀመድ፣ 64) ማማር አለምነው፣ 65) ምህረት አሞኜ፣ 66) ንብረት አሞኜ፣ 67) ዓባይ በላይ፣ 68) ቀሬ እረታ፣ 69) አነር፣ 70) አደም፣ 71) አንሙት፣ 72) አበበ፣ 73) ደምሴ፣ 74) ሞላ፣ 75) መሀመድ፣ 76) ካሳሁን አብዬ፣ 77) ሀሰን አልዩ፣ 78) ኦስማን ሰይድ፣ 79) መሀመድ አደም፣ 80) ሀሰን መሀመድ፣ 81) ጌታቸው፣ 82) ሞገስ መኮንን፣ 83) አህመድ አሊ፣ 84) አማረ መኮንን፣ 85) መኩሪያው አበረ፣ 86) ደሳለኝ ዳውድ፣ 87) ኡስማን ካሳው፣ 88) አለቤ ወዳጆ፣ 89) ሀብታሙ ጫኔ፣ 90) ተምትም አገኘሁ፣ 91) ካሳ ከበደ፣ 92) አዲሱ ሞንጋሴ፣ 93) አስቻለ ይሁን፣ 94) ቄስ ስመኘው ዘውዴ፣ 95) ፋጢ አሊ፣ 96) ጥበቡ አብጤ፣ 97) ጣሂር አበበ፣ 98) ኡስማን አሊ፣ 99) እስማኤል ደሳለኝ፣ 100) የኑስ መሀመድ፣ 101) ዚነት ሰይድ፣ 102) ሽኩር መሀመድ፣ 103) ፋጢማ ጅብሪል፣ 104) ሰሚራ ሰይድ፣ 105) ቄስ ሀብቴ፣ 106) ይልቃል ፍሬው፣ 107) ቀሜ ውበቱ፣ 108) ሸጋው ፈንቴ፣ 109) መሌ አራጋው፣ 110) ሀይማኖት አታላይ፣ 111) አሰፋ ሞኝነት፣ 112) ግዜው ፍቅሬ፣ 113) ሀብታሙ ተምትም፣ 114) ደሳለው ጌቱ፣ 115) ደምቤ በላይ፣ 116) አደም አንለይ፣ 117) ካሳሁን እምቢ አለ፣ 118) ሀብታሙ ደመቀ፣ 119) አዲሱ ያለው፣ 120) ዘውዱ ሽቴ፣ 121) አቡሃይ አለሙ፣ 122) አለማዬሁ አደም፣ 123) አበበ ያረጋል፣ 124) አሞኜ ብርሌ፣ 125) ኢብራሂም ሀሰን፣ 126) ሁሴን መሀመድ እና 127) ሳሙኤል ሞላ ይጠቀሳሉ። ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከተገደሉት መካከል:_ 128) ሙሉ እንድሪያስ፣ 129) አዳኑ ሞላ፣ 130) ቢስጢር ሀሰን፣ 131) መሀመድ ጅብሪል፣ 132) አዳነ አሰፌ፣ 133) ሰይድ አለም፣ 134) ኢሳ አህመድ፣ 135) ጦይብ አለሜ፣ 136) ልዬው ክብረት፣ 137) ጋሻው ኡመር፣ 138) ባቡሽ መሀመድ፣ 139) ኢብራሂም ገዜ፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የቆሰሉ:_ 140) ሀሰን ዳኘው፣ 141) ሀብቴ ስጦታው፣ 142) አህመድ ይመር፣ 143) ወርቁ በዜ፣ 144) ታዬ ጌታ፣ 145) ሀብታሙ ጥላሁን፣ 146) ሞገስ ደሴ፣ 147) አማረ ታደሰ፣ 149) ሙላት ብርሃን፣ 150) ቶፊቅ በላይነው፣ 151) አህመድ ኩሜ፣ 152) እሚያምረው መልኬ፣ 153) አስናቀው ሰጣርጌ፣ 154) ወርቁ ጌታቸው፣ 155) አህመድ ኩሜ፣ 156) አስኔ ሽመልስ፣ 157) ሙራድ ቸኮል፣ 158) ዳውድ ዘነበ፣ 159) መሀመድ ሙስጦፋ፣ 160) ገደፋ አያሌው፣ 161) አበራ የሻነህ፣ 162) መንገሻ ቀራለም፣ 163) ስዩም ፈለቀ፣ 164) ይበልጣል እንዬው፣ 165) ማሞ ጋሻው፣ 166) ክንዱ ስጦታው፣ 167) ያሲን መኩሪያው፣ 168) አወል ተመቸው፣ 169) የማታው፣ ታግተው አድራሻቸው የጠፋ:_ 170) ከማል አለባቸው፣ 171) ሙሉጌታ ገደፋው፣ 172) ሞላ በላይ፣ 173) ኡመር አደም፣ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply