በምስራቅ ወለጋ ኪረሞ ወረዳ ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ ተፈፀመ! ሕዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ተወላጅ የሆኑ የግፍ እስረኞችን ከኪረሙ ወረዳ ወደ ነቀምት…

በምስራቅ ወለጋ ኪረሞ ወረዳ ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ ተፈፀመ! ሕዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ተወላጅ የሆኑ የግፍ እስረኞችን ከኪረሙ ወረዳ ወደ ነቀምት አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በህዝብ ተቃውሞ መክሸፉ ይታወቃል። ህዝቡን እና ለማፈን የመጡ የታጠቁ የክልሉ ሀይሎችን በሀገር ሽማግሌዎች እና በሀይማኖት አባቶች ለማግባባት ቢሞከርም መስተዳድሩ ፍቃደኛ ከመሆን ይልቅ ባሰማራው ልዩ ኃይል አማካኝነት ጥያቄ ባቀረቡት ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት በማድረሱ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ይህን ተከትሎም የኪረሞ ወረዳ ከጊዳ አያና ወረዳ በአንድ ሲኖትራክ የተጫነ በዩኒፎርሙ የተለዬ አዲስ የታጠቀ ኃይል ወደ ኪረሞ በማስመጣት መሀል ከተማ ላይ ተኩስ እንዲከፈት አድርጓል። ያስመጡት ኃይልም ከተማ ላይ ያገኘውን አማራ እየተኮሰ መግደል መጀመሩን ተከትሎ ሚሊሾችን ጨምሮ ከ35 በላይ አማራዎች እንደተገደሉ ተመልክተናል ሲሉ የአሚማ ምንጮች ገልፀዋል። ትዕላንት አመሻሹንም 6 መኪና ሙሉ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ ኪረሞ ሲጓዝ አይተናል የሚሉት የአሚማ ምንጮች አማራዎችን ሊያጠቁ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል። በመጨረሻም በየጫካው እየተሳደዱ የሚገኙ አማራዎች ከነቀምት መከላከያ መጥቶ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቅርበዋል ሲል አሚማ ዘግቧል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply