በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ የጉሙዝ ተወላጆች የሽፍታ ቡድን_ቤኒን በአማራዎች ላይ ግድያ እና ዝርፊያ ፈጽሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ የጉሙዝ ተወላጆች የሽፍታ ቡድን_ቤኒን በአማራዎች ላይ ግድያ እና ዝርፊያ ፈጽሟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ በከማሽ ዞን አዋሳኝ ከሆነው ከሚዥጋ ወረዳ በዴሳ የመጡ የጉሙዝ ተወላጆች የሽፍታ ቡድን_ቤኒን ህዳር 7/2015 አመሻሹን በአማራዎች ላይ ግድያ እና ዝርፊያ ፈጽሟል። ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር እየተባበረ ለግድያ፣ለወረራ፣ ለዝርፊያ እና ለመሰል ጥፋት እየተንቀሳቀሰ ያለው የቤኒን ቡድን በሊሙ ወረዳ መንደር 8 እና መንደር 9 በሚባሉ አካባቢዎች ነው ጥቃቱን የፈጸመው። በዚህም አንድ የአማራ አርሶ አደርን በጥይት መግደሉን፣ ሁለተኛም ሌላ አንድ አርሶ አደርም ማቁሰሉን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ከስፍራው ነግረውናል። ከተመቱት መካከል አንደኛው በጥይት እንደተመታ በጫካ ሮጦ በመግባቱ ያለበትን ሁኔታ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም፤ ጫካው አስቸጋሪ እና ለመንቀሳቀስም የሰላሙ ሁኔታ ከባድ በመሆኑ ቆስሎም ከሆነ ለህክምና፣ ሞቶም ከሆነ አስከሬኑን ገና ለማንሳት አልተቻለም ተብሏል። በሊሙ አርቁቢ መንደር አንድ የአማራዎችን ቤቶች እያፈረሱ ቆርቆሮውን እየነቀሉ በመውሰድ ላይ ሳሉ በተሰጣቸው የአጸፋ ምላሽም ከቡድኑ አንድ አባሉ የተገደለበት ሲሆን የዘረፉትን ብዙ ንብረትም ለማስቀረት መቻሉን እና እንዲሸሹ መደረጉም ተገልጧል። ይህን ተከትሎም በርካታ የአማራ ተወላጆች ከሊሙ መንደር 8 እየተፈናቀሉ መሆናቸው ተሰምቷል። የመንደር 9 እና 10 አካባቢዎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ለተፈናቃዮች ትብብር እንዲያደርጉላቸው ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply