በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሞ ገሊላ ወረዳ በመልካለሜ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አንድ አባት በጥይት ሲገደሉ ቤተሰቦቻቸው አምልጠዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 15…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሞ ገሊላ ወረዳ በመልካለሜ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አንድ አባት በጥይት ሲገደሉ ቤተሰቦቻቸው አምልጠዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 15…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሞ ገሊላ ወረዳ በመልካለሜ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አንድ አባት በጥይት ሲገደሉ ቤተሰቦቻቸው አምልጠዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሞ ገሊላ ወረዳ በመልካለሜ ቀበሌ በዴሳደሴ በተባለ ጎጥ የሚኖሩ አቶ ምትኩ ነጮ የተባሉ አባት በጥይት ሲገደሉ ቤተሰቦቻቸው ከጥቃት አምልጠዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ግድያው የተፈፀመው ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ሲሆን በወቅቱ ሟች አቶ ምትኩ ነጮ በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ እንደነበሩ ተገልጧል። በቤት ውስጥ የነበሩ የሟቹ ቤተሰቦችም ሸሽተው ወደ ጫካ በመግባት በህይወት ተርፈዋል ያሉት ምንጫችን ይህን ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ አማራዎች ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ገብተዋል ሲሉ ተናግረዋል። ግድያውን የተፈፀመው ማታ ስለሆነ ለመለየት ብንቸገርም በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው ምንጫችን የተናገሩት። የልጆች አባት የሆኑት የአቶ ምትኩ ነጮ ስርዓተ ቀብርም ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአካባቢው ባለ መድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርቡ በኦነግ ሸኔና ተባባሪዎቹ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የተፈፀመበት የጊዳ ወረዳ አዋሳኝ የሆነው ሊሞ ገሊላ ወረዳም ስጋት አለበት። በመሆኑም የፌደራል መንግስት ለአካባቢው ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply