You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገው ግድያ ቀጥሏል፤ በጊዳ አያና ወረዳ የ7 ልጆች አባት በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በጥይት ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገው ግድያ ቀጥሏል፤ በጊዳ አያና ወረዳ የ7 ልጆች አባት በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በጥይት ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገው ግድያ ቀጥሏል፤ በጊዳ አያና ወረዳ የ7 ልጆች አባት በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በጥይት ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገው ግድያ ቀጥሏል፤ በጊዳ አያና ወረዳ የ7 ልጆች አባት የሆኑት አቶ መልኩ ወርቁ አማራዊ ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በትሕነግ አባላት በጥይት ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። ግድያው የተፈጸመው በመንደር 5 ታህሳስ 12 ቀን 2014 ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ በሩን ሰብረው በገቡ የአሸባሪው ትሕነግ አባላት ነው ተብሏል። ገዳዮችም የሟችን አስከሬን ከመንደር 5 ወደ መንደር 6 እየጎተቱ በመውሰድ በአንድ መጋዝን አካባቢ ጥለውት መገኘቱ የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል። በቤታቸው ውስጥ የነበረ 10 ሽህ ብርም በገዳዮች ተዘርፎ ተወስዷል። ለነፍሴ ያሉ አንድ ሰው ተደብቀው የሟችን አስከሬን ሜዳ ላይ ቆፍረው አፈር ያለበሱት መሆኑ ተሰምቷል። በተያያዘ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዋዩጡቃ ወረዳ ተፈናቅለው በጉቴ የሚገኙ ከ10 ሽህ 250 በላይ የሚሆኑ አማራዎችን በመወከል ወደ ነቀምት ለአቤቱታ ያቀኑ 3 ተወካዮች መስተዳድሩ የለም በሚል ያለፍትህ ወደ ወረዳው መመለሳቸውን ተናግረዋል። ከአንገር ጉትን በቅርብ ርቀት መንደር 4 መውጫ እንጅሮ በተባለ ወንዝ አካባቢ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በተደጋጋሚ ጥይት በመተኮስ የአማራዎች አዝመራ እንዳይሰበሰብ መከልከሉ ተገልጧል። ኦሮሚያ በሚባለው ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ለከት የለሽ ግፍ እየተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ የወገን ያለህ ድረሱልን የሚል ጩኸት መሰማት ከጀመረ የከረመ ቢሆንም በመንግስት ዘንድ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሏል የሚሉት በርካቶች ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply