You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ የመንደር 8 ቀበሌ ነዋሪዎች ከአሸባሪዎች ጥቃት ታደጉን ሲሉ የድረሱልን ጥሪ አሰሙ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ የመንደር 8 ቀበሌ ነዋሪዎች ከአሸባሪዎች ጥቃት ታደጉን ሲሉ የድረሱልን ጥሪ አሰሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በሊሙ ወረዳ የመንደር 8 ቀበሌ ነዋሪዎች ከአሸባሪዎች ጥቃት ታደጉን ሲሉ የድረሱልን ጥሪ አሰሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥቅምት 8/2015 ከምስራቅ ወለጋ ዞን ከሊሙ ወረዳ ከአርቁምቢ መንደር 3 ከሶስቱም የፅንፈኛች ቡድን የተሰባሰበው ኃይል ወደ መንደር 8፣ 9 እና 10 ለመግባት እየሞከረ ነው ተብሏል። “እባካችሁ የመንግስትና የአከባቢው ማህበረሰብ ወደ መንደር 8 በመግባት ሊያግዘን ይገባል” ሲሉ ነዋሪዎች ጥሪ አድርገዋል። በሰሞኑ ወደ አንገር ጉትን ለመግባት በግልፅ ሲፎክር ከነበረው ከአሸባሪው ሸኔ ጋር በመተባበር በጋራ የህወሓት ሐይሎች እና የቤኒን ታጣቂዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን በያሶ ወረዳ ከበዴሳ ቀበሌ ከሚገኘው የፅንፈኞች ካምፕ በመነሳት አርቁምቢ መንደር 3 የተሰባሰበው ኃይል ለመግባት ያሰበው በጋራ ሆኖ አንገር ጉትን ከተማንና የዙሪያዋን ከተማ ለመውረር ነው ሲሉ ተናገረዋል። “ሁሉም በአስቸኳይ ወደተጠቀሰው ቦታ በመትመም ሊያግዘን ይገባል” ሲሉ የድረሱን ጥሪ አቅርበል። መረጃው_የአንገር ጉትን ልዩ ዞን ጥያቄ (የአጉልዞ ጥያቄ) ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply