You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዘር ተኮር ጥቃቱን እንደቀጠለበት ነው፤ አንድ የአማራ አርሶ አደርን በማገት ቤተሰቦችን 200 ሽህ ብር…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዘር ተኮር ጥቃቱን እንደቀጠለበት ነው፤ አንድ የአማራ አርሶ አደርን በማገት ቤተሰቦችን 200 ሽህ ብር…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዘር ተኮር ጥቃቱን እንደቀጠለበት ነው፤ አንድ የአማራ አርሶ አደርን በማገት ቤተሰቦችን 200 ሽህ ብር እንዲከፍሉ ጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሼ ዞን የበለው ጅጋንፎይ ነዋሪ የሆኑት አቶ አዱኛ ጥላሁን መስከረም 3 ቀን 2013 ከሶጌ ከተማ ተነስተው በነቀምት በኩል ከአካባቢው ለመውጣት እየተንቀሳቀሱ ሳለ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ፋሲጋ ወረዳ በለው አንገር አካባቢ ታፍነው መወሰዳቸው ተገልጧል። መታገታቸው የታወቀው ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2013 ሲሆን ቤተሰብ 200 ሽህ ብር እንዲከፍል በዘራፊውና ዘር አጥፊው ቡድን መጠየቁ ተሰምቷል። እስከ 100 እና 50 ሽህ ሽር ድርድር መገባቱ የተገለፀ ሲሆን ገንዘቡ ገቢ የሚደረግበት አካውንትም “ሌሊሳ ተመስገን” በሚል ስም መከፈቱን ለማወቅ ተችሏል። ዘር እና አጥንት እየቆጠረ ባለው አሸባሪው፣ ተስፋፊውና ወራሪው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ ተገቢ የሚባል እርምጃ እየተወሰደበት ባለመሆኑ በኦሮሚያ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ባንዴራ እስከማውረድና መንገድ እስከመቁረጥ ደርሷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply