You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸም ጥቃት 200 ንፁሀን  በአስቃቂ ሁኔታ ተገደሉ  ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸም ጥቃት በርካቶች በአስቃቂ ሁ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸም ጥቃት 200 ንፁሀን በአስቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸም ጥቃት በርካቶች በአስቃቂ ሁ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸም ጥቃት 200 ንፁሀን በአስቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸም ጥቃት በርካቶች በአስቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገግረዋል።በኪረሙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ብሄራቸው እየተለየ ተገድለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ተጨማሪ እልቂትን ሽሽት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅተዋል፡፡ የሰሞኑ ግጭት መንስኤ በኪረሙ በእስራ ላይ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ግድያ መሆኑን ከአንገር ጉቴ ሸሽተው ስቡንሱሬ ቀበሌ የሚገኙ ስማቸው እንዳይጠቅሰ የፈለጉ ነዋሪ ተናግረዋል። “የመንግስት አካላት ሸኔ ይገድላችኋል ኑ ወደ ካምፕ ግቡ በማለት የአማራ ገበሬዎችን ስብስበው ኪረሞ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ አስረዋቸው ነበር፤ ሽማግሌዎች የታሰሩት እንዲፈቱ ጥረት ቢያደርጉም ኦሮሞዎች እየተለቀቁ አማራዎች ግን እንዳይወጡ ተደርጓል” የሚሉት አስተያየት ሰጪው የሰሞኑ ችግር መንስኤም ከዚሁ ጋር ይያያዛል ብለዋል። እኝህ ነዋሪ በእስራ ላይ የነበሩትን የአማራ ተወላጆች ጊዳ ወደ ተባለ ቦታ አግቶ ለመውሰድ የተደረገው ጥረትም የአማራ ተወላጆችን ከኦሮሚያ ልዩ ሃይል ጋር እንዲጋጩ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ቅዳሜ ህዳር 24/2015 ማለዳ ላይ የተጀመረው ጥቃትም ከ200 በላይ የአማራ ተወላጆችን ህይወት መቅጠፉንና በርካቶችም መቁሰላቸውን ነዋሪው ጨምረው ተናግረዋል። “ከነቀምቴ በርካታ የኦሮሚያ የጸጥታ ሃይል ወደ ጉቴን እየመጣ ነው” መባሉም በከተማዋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የመኖሪያ ቤታቸውን ለቀው በጫካ ውስጥ እንዲደበቁ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡የኪረሙን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ “አማራው ለቆ ወደ ሃሮ፤ ኦሮሞው ደግሞ ወደ ጊዳ አያና ሸሽቷል” የሚሉት የአይን እማኙ፤ ህፃናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ህይወታችንን ለማትረፍ በመሰደዳቸው ጉትን ሰው አልባ ሆናለች ብለዋል። ነዋሪው አንገር ጉቴ ላይ ብቻ 56 ሰዎች መቀበራቸውን እና በየጫካው የሟቾች ፍለጋው ስለቀጠለም ቁጥሩ ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ሌላኛው የአንገር ጉቴ ከተማ ነዋሪ በነበረው ችግር የኦሮሞ ተወላጆችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ለአል አይን ገልጸዋል። እስካሁን ሁለት ኦሮሞዎች መገደላቸውን አውቃለሁ የሚሉት የአይን እማኙ፣ ግድያን ሽሽት የአንገር ጉቴ ከተማ የኦሮሞ ተወላጆችም ወደ ነቀምትና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው ከተማዋ ባዶ ሆናለች ብለዋል።“ፋኖ ተደራጅቶ ሊወጋችሁ እየመጣ ነው” የሚል መረጃ መሰራጨቱም ህዝቡን ሽብር ውስጥ መክተቱን ተናግረዋል። በአካባቢው እየተፈጸመ ስላለው ግድያ አስመክቶ የፌዴራሉም ሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እስካሁን ያሉት ነገር የለም። ምንጭ፦ አል አይን

Source: Link to the Post

Leave a Reply