በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ ከ17 መኪና በላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሌሊት መግባቱ አማራውን ለከፍተኛ ስጋት መዳረጉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 6 ቀን 2014…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ ከ17 መኪና በላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሌሊት መግባቱ አማራውን ለከፍተኛ ስጋት መዳረጉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሀምሌ 5/2014 በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን ከተማ ከ17 መኪና በላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሌሊት መግባቱ ተሰምቷል። የአንገር ጉትን ልዩ ዞን ጥያቄ (አጉልዞ) እንዳጋራው በአንገር ጉትን ከተማ በአራቱም መግቢያ እና መውጫ በሮች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተዘግቷል። ነዋሪዎችም ያለአንዳች መረጃ በሌሊት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መግባት ትጥቅ ለማስፈታትና ለኦነግ ሸኔ ለማደላደል እንዳይሆን በሚል ለከፍተኛ ስጋት መዳረጋቸው ታውቋል። ስለሆነም በሰሞኑ በተፈጠረው የትጥቅ የማስፈታት እና የማዋከብ ዘመቻን ተከትሎ ልዩ ኃይሉ በ17 እና ከዛም በላይ በሚሆን ተሽከርካሪዎች ተጭኖ መግባቱ ለዚህ አላማ ላለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ያልቻለው ህዝብ ከመንግሥት በኩል ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጠው እየጠየቀ ነው ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply